1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

 የሱዳን ከፍተኛ ልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ

እሑድ፣ ኅዳር 14 2012

ሰሞኑን ወደ ኢትዮጵያ የተጓዘው የሱዳን ከፍተኛ ልዑካን ቡድን ከኢትዮጵያ አቻው ጋር በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተገኝቶ የወዳጅነት ሀሳብ ተለዋውጧል። ይፋዊ የሶስት ቀናት ጉብኝቱንም ዛሬ በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል።

Sudanesische Delegation in Äthiopien |  Hirut Zemene
Sudanesische Delegation in Äthiopien | Hirut Zemene
ምስል፦ DW

This browser does not support the audio element.

የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ በስፍራው ተገኝቶ እንደዘገበልን የሁለቱን ሀገራት ወዳጅነት የሚያጠናክሩ ነጥቦች በመክፈቻ ንግግር ላይ ተነስተዋል። የዚሁ ልኡክ አባል የሆኑትም ሱዳናዊ ፕሮፌሰር ኢብራሂም ዳጋሽ  ወደ ሀገራቸው እንደ ኢትዮጵያ ካሉ በስተምስራቅ ከሚገኙ ሀገራት ተሰደው በቀን ሰራተኝነት የሚያገለግሉትን ሰዎች « የአንድ ሀገር ሰዎች ነን» እና እነሱን እንደ ችግር ማየት አይገባም ሲሉ በተለይ አዲስ የተሾሙትን የሱዳን የሀገር ውስጥ ሚኒስትር መውቀሳቸውን ተናግረዋል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ልደት አበበ

 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW