የሱዳን የርስበርስ ጦርነት እንዲቆም የሚደረገዉ ግፊትና ጫና
ሐሙስ፣ ሚያዝያ 9 2017
የሱዳን የርስበርስ ጦርነት አሁንም ለሶስተኛ ዓመት እንደቀጠለ ነዉ።ጦርነቱ በብዙ ሺሕ የሚቆጠር ሕዝብ ፈጅቷል።ከ13 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ አሰድዷል ወይም አፈናቅሏል።ሱዳን ዉስጥ አስቸኳይ ሰብአዊ ርዳታ የሚፈልገዉ ሕዝብ ቁጥር ከ20 ሚሊዮን በልጧል።ተፋላሚ ኃይላት ጦርነቱን በድርድር እንዲያቆሙ የተለያዩ ወገኖች ቢጠይቁም እስካሁን ግን ጥያቄ፣ግፊትና ጫናዉ ተቀባይነት ያገኘ አይምስልም።በያዝነዉ ሳምንት ለንደን ዉስጥ ተሰብስበዉ የነበሩት የተለያዩ ሐገራትና የርዳታ ድርጅቶች ተጠሪዎች ግን ጦርነቱ እንዲቆም በድጋሚ ጠይቀዋል።
ከሁለት አመታት በላይ የዘለቀውን በሱዳን የቀጠለውን ደም አፋሳሽ ግጭት ለማስቆምና ህዝቡ ሰብአዊ እርዳታ የሚያገኝበትን ሁኔታ መፍትሄ ለመሻት የ17 አገራት ተወካዩችና አምስት መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅት ተወካዎች በጉባኤው ላይ ተሳትፈዋል። ጉባኤውን የመሩት የብሪታኒያ የውጭ ገዳይ ሚኒስትር ሲሆኑ የጀርመን መንግስትን በመወከል ደግሞ የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር አናሊና ባይቡርክ ተገኝተዋል።የብሪታንያዉ የውጭጉዳይ ሚንስትር ዴቪድ ላሚ ባደረጉት ንግግር ይህ እልቂት ያለ ማቋረጥ መቀጠሉ እጅግ የሚያሳዝን እና ተገቢም እንዳልሆነ ገልፀዋል።
ሁላችሁንም በጉባኤው ተሳታፊነት መፍትሄ ከመሻት በመምጣታችሁ ምስጋናዪን አቀርባለሁ።እንግዲህ ሁለት አመት ሙሉ ምንም መፍትሄ ያልተገኘለት ህዝብጠየሚያጫርሰውን ደም አፋሳሹ ህፃናትን እናቶችን አእና አቅመ ደካሞችን ተፈጀውን የርስ በርስ ጦርነት በእንዲህ ሁኔታ ማየት ተገቢ አይደለም፣ አሁን መፍትሄ ለመፈለግ እዚህ ተገናኝተናል ሀላችንም በጋራ ማድረግ የሚገባንን ነገር አድርገን ይሄ ጦርነት በአፋጣኝ መቆም አለበት
የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አናሊና ባይቡከርም ከ ዴቪድ ላሚ በመቀጠል አስተያየታቸውን ሰጥተዋል የተከበሩ። አቶ ዴቪድ የተከበራችሁ ተሳታፊ ሚንስትሮች እዚህ ቦታ ላይ ስለተሰበሰብን አመሰግናለሁ። ዛሬ አንድ ምነግራችሁ ታሪክ አለ አንድ በህመም ሆስፒታል ውስጥ ስለተሰቃየ ልጅ በጦርነቱ ምክኒያ ሙሉ ህክምና ማግኘት ሳይችል ቀርቶ የሞተ ነው
ለናቱ ምን አላት ሆዴን አሞኛል እናቴ ቶሎ ድኜ ውጭ ወጥቸ መጫወት እችላለሁ ከጓሰኞቼ ጋር ነበር ያላት ከጥቂት ደቂቃዎች በውሀላ ግን ህይወቱ አልፏል። ይህ ቨአሁኑ ሰአት በብዙ የሱዳን ቤተሰቦችና የሱዳን ልጆች እናቶች አቅመደካሞች ላይ እየደረሰ ያለ ችግር ነው
ለዚህ ችግር ተሯሩጠን መፍትሄ መፈለግ የሁላችንም ሀላፊነት ነው።ዴቪድ ላሚ አያይዘው ያለውን ችግር ሲገልፁእዚህጋ ትልቁ እንቅፋት የእርዳታ ማነስ ወይም ደግሞ የረጅዎች አለመሳተፍ አይደለምዋናው ትልቁ እንቅፋት አሁን የ ፖለቲካ ፈቃደኝነት ነው።
መኮንን ሚካኤል
ነጋሽ መሐመድ
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር