1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

«የሱዳን ጉዳይ የሚሻው ዲፕሎማሲ ነው»የዲፕሎማሲ አዋቂዎች

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 7 2014

ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር የምትዋሰንበት ድንበር ላይ ከሰሞኑ ተጨማሪ ወታደሮችን ማስፈሯ ተነግሯል። በዚህ ጉዳዩ ላይ ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸው ሁለት የዲፕሎማሲና ቀጣናዊ ጉዳይ አዋቂዎች ኢትዮጵያ አሁንም የሱዳንን ጠብ አጫሪ ርምጃ በሰከነ ዲፕሎማዲያዊ አማራጭ ብቻ እንድትመለከተው ጠይቀዋል።

Äthiopien Sudan Grenzgebiet Landwirtschaft
ምስል፦ Alemnew Mekonnen/DW

ሱዳን ከሰሞኑ ተጨማሪ ወታደሮችን ማስፈሯ ተነግሯል

This browser does not support the audio element.

ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር የምትዋሰንበት ድንበር ላይ ከሰሞኑ ተጨማሪ ወታደሮችን ማስፈሯ ተነግሯል። በዚህ ጉዳዩ ላይ ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸው ሁለት የዲፕሎማሲና ቀጣናዊ ጉዳይ አዋቂዎች ኢትዮጵያ አሁንም የሱዳንን ጠብ አጫሪ ርምጃ በሰከነ ዲፕሎማዲያዊ አማራጭ ብቻ እንድትመለከተው ጠይቀዋል። ሱዳን የውስጥ ጉዳይዋን በኢትዮጵያ ላይ ጦር በመስበቅ ለማለዘብ ጥረት ማድረግን ከመምረጧ ባለፈ የግብጽ እና የምዕራቡ ዓለም ተጽእኖም ይህን መሰል ድርጊት ውስጥ እንድትገባ ማድረጉን ተንታኞቹ ገልፀዋል። በሌላ በኩል ሱዳን ወደ ኢትዮጵያ ተጨማሪ ጦር የማስጠጋቷ ምክንያት ምዕራባዊያኑ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ያሰቡት ባለመሳካቱ በምዕራብ ኢትዮጵያ በኩል ሕወሓትን ለመደገፍ የያዙት ውጥን አካል ሊሆን ስለሚችል መንግሥት ጥንቃቄ እንዲያደርግ መክረዋል። የሁለቱ አገሮች የድንበር ይገባኛል ጥያቄ ወደፊት ቢቻል በሁለቱ ጎረቤት አገሮች ውይይት ካልሆነም በቀጣናዊ እና አለምአቀፋዊ ድርጅቶች ድጋፍ ሊፈታ እንደሚችልም ባለሞያዎቹ ገልፀዋል። ለዚህም ዘገባ ሰለሞን ሙጬ ከአዲስ አበባ።

ሰለሞን ሙጬ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW