የሱዳን ግጭት ዳፋ ለአውሮጳ ኅብረት
ሐሙስ፣ ሚያዝያ 12 2015
በሱዳን የጦር ሠራዊት እና የፈጥኖ ደራሹ ኃይል መካከል ዛሬም የቀጠለው ውጊያው እንዳሳሰባቸው በርካታ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ አባላት ገልጠዋል ። የአውሮጳ ኅብረት ከሁሉም በላይ በካርቱም የሚገኙ የአውሮጳ ኅብረት ዜጎችና የዓለማቀፍ ድርጅቶች ሠራተኞች ደህንነት ያሳስበናል ብሏል ። የጀመን መንግሥት ዜጎቹን ትናንት በጦር አውሮፕላን ለማውጣት አቅዶ በሱዳን ችግር የተነሳ ልዩ በረራውን መሰረዙ ተዘግቧል ። የግጭት እና ቀውስ ተንታኞች፦ ሁለቱ የሱዳን የጦር ክፍሎች በየራሳቸው እያደጉ በመሄዳቸውና የአዛዦቻቸውም የፖቲለካ ፋላጎት በመኖሩ በቀላሉ መስማማት መቻላቸው አጠራጣሪ ነው ይላሉ ።
በሱዳን ባለፈው ቅድሜ በመከላከያ ሰርዊቱና በፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ መክከል የተጀመረው ውጊያ በተለይ በዋና ከተማ ካርቱም አሁንም ተጠናክሮ ቀጥሏል ። በጦርነቱ እሳክሁን ከ300 በላይ ሰዎች እንድተገድሉና ከ ሁለት ሺ ስድስት መቶ በላይ ደግሞ እንደቆሰሉ ከልዩ ልዩ ድርጅቶች የሚውጡ ዘገባዎች ያስረዳሉ። ሆስፒትሎችና ሀኪም ቤቶች፤ በጦርነቱ ጉዳት ስለደረስብቸውና የውሀና መብራት አገልግሎቶች ስለተቋረጡባቸው አገልግሎት መስጠት አልቻሉም ነው የሚባለው ። ሱቆችና የምግብ መድብሮች በመዘጋታቸውም የካርቱም ህዝብ በተለይ በዚህ የሮመዳን ወቅት ለከፍተኛ ችግር እንደተጋለጠ ነው የሚታወቀው። አንዳንድ ዲፕላማቶችና የዕርዳታ ሰጭ ድርጅቶች ሰራተኖችም ጥቃት እንደደረሰባቸውና የቆሰሉም እንዳሉ የተገለጸ ሲሆን፤ እስክሁን አንድም አገር ዜጎቹን ከሱዳን ማስወጣት እንዳልቻለ ነው የሚገለጸው።
እ.እ.እ በ2019 ዓም ሕዝባዊ ተቃውሞ ያየለባቸውን ኦማር አልበሺርን ከስልጣን ያስወገዱት የሱዳን የጦር ኃይሎች፤ ቆይቶ ደግሞ የጠቅላይ ሚኒስተር ሀምዶክን የሽግግር የሲቪል መንግስት በማስወገድ ስልጣኑን ተቆጣጥረው ቆይተውል፤ የመክለከያ ሰራዊቱ ዋና አዛዥ ጀነራል ቡህራን ፕሬዝዳንት፤ የፈጥኖ ደራሹ ዋና አዛዥ ጀኔራል ሞሃመድ ሃምዳን ዳግሎ ደግሞ ምክትል ፕሬዝዳንት በመሆን። ሁሉም ስልጣናቸውን በዚህ ወር መጨረሻ ወደ ሲቪል አስተዳደር ለመመለሰ ተማምተው፤ የሺግግር የሺቭል መንግስት ዳግም ሊመሰረት ነው ተብሎ ሲጠበቅ ባለፈው ቅድሜ ይህን የመሰለ ጦርነት መከፈቱ የሱዳንን ፖለቲክ አይገመቴነት የሚያረግግጥ ሁኗል ።
ችግሩ ያለው በሁለቱ የጦር አዛዦች መካከል ያለው የስልጣን ፉክክር ነው የሚሉት ታዛቢዎች፤ ሁለቱ ጀነራሎች ተስማምተው በጋራ ለመስራት ወይም ጥቅም ፍላጎታቸውን ለሰላም ሲሉ አሳልፎ ለመስጠት ያላቸውን ፍላት አብዝተው ይጠራጠራሉ ። ሁለቱን ሀይሎች ወደ ጦርነት ያስገባቸው መነሻ ምክኒያት የፈጥኖ ደራሹ ሀይል ወደ መከላከያ ሰራዊቱ የሚገባበት የግዜ ሰሌዳ ነው ቢባልም፤ ዋና የችግሩ ምንጭ ግን በአንድ አገር ውስጥ ሁለት ተገዳዳሪ የጦር ሰራዊት ሀይል መገንባቱ እንደሆነ ነው የሚታመነው።
የክራይሲስ ግሩፕ የአፍሪካ ቀንድ ዳይሬክተር ሚስተር አላን ቦዝዌል እንደሚሉት፤ ሁለቱ የጦር ክፍሎች በየራሳቸው እያደጉ በመሄዳቸውና የአዛዦቻቸውም የፖቲለካ ፋላጎት በመኖሩ በቀላሉ መስማማት መቻላቸው አጠራጣሪ ነው። “ የፈጥኖ ድራሹ ወደ ሰራዊቱ ሊዋሀድ በሚችልበት የግዜ ሰሌዳ ላይ ሊስማሙ መቻላቸው አጠርጣሪ ነው ምክኒያቱም፤ ጦሩ፤ የፈጥኖ ደራሹ ሀይል እያደገ መሄዱንና አዛዡ፤ ጀነራል ሀምዳን የፖለቲካ ስልጣን ፍላጎት እንዳላቸው በመገንዘብ በፍጥነት ወደ ሰራዊቱ እንዲካተት የሚፈልግ ቢሆንም ይህ ግን ቀላል አለሆነም በማለት ጀነራል ሀምዳን ፋላጎታቸውን ለማሳክት የራሳቸውን ዝግጅት ሳያደርጉ እንዳልቀሩ መገመት እንደሚቻል አስረድተዋል ።
ባለፉት ቀናት በጦርነቱ የደረሰው ጉዳትና በተፋላሚ ወገኖች እየታየ ያለው መካረር፤ ሱዳንን ወደ ፍጹም ቀውስ እንዳይስገባት የሚይሰጋ ሁኗል። እስካሁን ከበርክታ አገሮችና መንግስታት ለሁለቱም ወገኖች የሚቀርቡ የተኩስ ማቆም ጥሪዎች ሰሚ አላገኙም። ጀኔራሎቹም በህዝቡና አገራቸው ላይ እየደረሰ ያለው ጉዳትና ውድመትም የሚያሳስባቸው አልመሰለም። የሱዳን ወዳጅ አገሮችና አጋሮች በአሁኑ ወቅት ጦርነቱን ማስቆም ቀርቶ ዜጎችቸውን ማሰወጣት አልቻሉም። የአውሮጳ ኅብረት ከሁሉም በላይ በካርቱም የሚገኙ የአውሮጳ ህብረት ዜጎችና የዓለማቀፍ ድርጅቶች ሰራተኖች ደህንነት የሚያሳስበው መሆኑን ሲገልጹ ለነበሩት የኅብረቱ ቃል አቀባይ ወይዘሪት ናቢላ ዲደብሊው ከህብረቱ ዜጎች ደህንነት ባሻገር ጦርነቱ እንዲቆምና ሰላም እንዲሰፍን ኅብረቱ በተጨባጭ ምን እያደረገ እንደሆነ ጠይቋቸው ነበር፤ “ ልክ ነው በዚያ ስለሚገኙት ዜጎቻንና ሰራተኖቻችን ደህንነት ነው የምንናገረው ግን በሱዳን ህዝብ ላይ ስለደረሰው ሁሉም ያሳስበናል በማለት እስካሁንም ኅብረቱ የአካባቢውና ዓላምቀፍ ባለድርሻ አካላት፤ ሁለቱ ተፋላሚ ወገኖች ተኩስ እንዲያቆሙና ወደ ውይይት እንዲመጡ የሚያደርጉትን ጥረት በማስተባበር እየሰራ እንደሆነ ገልጸዋል።
በሱዳን የሚካሄደው ጦርነትና የሚከተለው ቀውስ በሱዳኖቹ ከሚያደርሰው ሁለንተናዊ ቀውስ አልፎ፤ በራሳቸው የውስጥ ችግርች ተተብትበው በተያዙት እንደ ኢትዮጵያ፣ ደብብ ሱዳንና ቻድ በመሳሰሉት ጎረቤቶቿም ከፍተኛ ችግር ሊያስክትል እንደሚችል የታመነ ነው።በርክታ ስደተኖችም ወደጎርቤት አገሮችና አውሮፓ ጭምር እንዲፈልሱ ሊያስገድድ እንደሚችል ከወዲሁ እየተነገረ ነው ።
ገበያው ንጉሤ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
እሸቴ በቀለ