የሱዳን ጦርነትና ድርድር
ረቡዕ፣ ግንቦት 2 2015
የሱዳን ተፋላሚ ኃይላት የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲያደርጉ ለማግባባት ጂዳ-ሳዑዲ አረቢያ ዉስጥ የተያዘዉ ድርድር እስካሁን ሁነኛ ዉጤት አላመጣም።ጄኔራል አብዱል ፈታሕ አል ቡርሐን የሚመሩት የሱዳን መከላከያ ሠራዊትና ጄኔራል መሐመድ ሐምዳን ዳግሎ (ሐሚቲ) የሚያዙት የሐገሪቱ ፈጥኖ ደራሽ ጦር የገጠሙት ዉጊያ አራተኛ ሳምንቱን አገባድዷል።በዉጊያዉ ወደ 6 መቶ የሚጠጋ ሰዉ መገደሉና ከ700 ሺሕ በላይ መፈናቀሉን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታዉቋል።የጂዳዉን ድርድር የሚከታተሉ ዲፕሎማቶች እንደሚሉት ሁለቱ ወገኖች ድጋፍ ከማሰባሰብ ሌላ እስካሁን ዉጊያዉን የማቆም ፍላጎት አላሳዩም።
በሁለቱ ተፍላሚ ወገኖች መካከል እስካሁን ከሰባት ግዜ በላይ የተኩስ ማቆም ስምምነት ተደርጎ የነበር ቢህንም አንዱም ተከብሮ እንደማይውቅ ነው የሚታወቀው። በአሁኑ ወቅትም በአሜሪካና ሳኡዲ አረቢያ አማካይነት የሁለቱ ጀነራሎች ተወክዮች ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ በጂዳ ለውይይት የተቀመጡ ቢሆንም፤ ጦርነቱ ግን እንደቀጠለ ነው፤ ሱዳናውያንም በገፍ ወደ ጎርቤት ገሮች እየተሰደዱ ነው።፡ በአሁኑ ወቅት በሱዳን በተለይም በካርቱም ያለውን ሰባዊ ቀውስ በክናዳ የሚጊል ዩንቨርስቲ ፖሮፊሰር የሆኑት ሱዳናዊው ካህሊድ ሙስተፋ መዳኒ እንደሚከተለው ገልጸውታል። “ አሁን ያለው ሰባዊ ቀውስ ሊነገር ከሚችለው በላይ ነው። ከመብራት፤ ከውሀና ከምግብ እጥረቱ አልፎ ዋና ከተማ ካርቱም ውስጥ እረህብ ገብቷል። በግል ቤቶች፤የመንግስት ተቁሞችና ፋብሪካዎች መጠነ ሰፊ ዝርፊያና ስርቆት እየተካሄደ ነው||” በማለት፤ ይህም አስቀያሚው የቀውሱ መገለጫ መሆኑን ገልጸዋል። ፕሮፈሰሩ አከለውም፤ በዚህ አስቸጋሪ ሁኒታ ውስጥ ሁነው ሰዎችን ለመርዳት የሚንቀስቀሱ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰጭ ወጣቶችና የሲቪክ ማህበራት አባሎች ላይ በሁለቱም ተፋላሚ ወገኖች ጥቃት የሚፈጸም መሆኑንም አስታውቀውል።
የጂዳውን ውይይት ያመቻቹት አሜሪካና ሳኡዲ አረቢያ አላማቸው፤ ሁለቱ ሀይሎች ቢያንስ የሰባዊ እርዳታ ለማስተላለፍ፤ ሲቪሎችን ከጥቃት ለመካላከልና ለዘላቂ ሰላም የሚረዱ አመቺ ሁኒታዎችን ለመፍጠር የሚያስችል የተኩስ አቁም ስምምነት ለመድረስ እንደሆነ በመግለጫዎቻቸው አስረድተዋል። የውይይቱ ሂደትና ተስፋው በምን ደርጃ ላይ እንደሆነ ግን እስካሁን የተገለጸ ነገር የለም።
ከዚሁ ጎን ለጎን የአረብ ሊግ የራሱን በሱዳን ሰላም እንዲሰፍን ጥረት የሚያደርግና ግብጽ፤ ሳኡዲ አረቢያና የሊጉ ዋና ጸሀፊ የሚገኙበት ኮሚቴ ማቁቋሙ ተገልጿል። ቀደም ሲልም የምስራቅ አፍርካ በየነ መንግስታ ኢጋድ በደቡብ ሱዳን መሪ ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር የሚመራና የጂቡቲና ኬንያ መሪዎች የተካተቱበት አስታራቂ ቡድን መመስረቱ የሚታወስ ነው።
ሱዳን፤የስሜን ዓፍሪካ፣ የሳህል፣ የምስራቅና የአፍርካ ቀንድ፤ እንዲሁም የገልፍ ባህር ሰላጤ አገሮች ጎረቤትና መተላላለፊያም በመሆኗ ሁሉም የየአካባቢው አገሮች፤ ሀያላን መንግስትቱ ጭምር ትኩረት የሚያደርጉባት ስትራቴጂክዊ አገር ነች። የፖለቲካ ተንታኖች እንደሚሉት ሁሉም በሱዳን ጥቅም አለኝ የሚሉ አገሮች ለሱዳን ችግር የጋራ የመፍትሄ ሀሳብ ያላቸው ሳይሆኑ ይልቁንም የየራሳቸውን ተጻራሪ ሊሆኑ የሚችሉ ሀሳቦች እንዲተገበሩ ወይም የሚደግፏቸው ቡድኖች ወደ ስልጣን እንዲመጡ የየግላቸውን ጥረት የሚይደርጉ ንቸው። በጅዳ እየተካሄደ ያለው ውይይትም ከጅምሩ የሚመለክታቸውን ሁሉ ያላከተተና የአዋያዮቹን ፍላጎት ብቻ ያማክለ በመሆኑ ውጤት ማስገኘቱን እነዚሁ ተንትኞች ይጠራጠራሉ። ሱዳናዊው ፕሮፈሰር ካህሊድ ሙስተፋ እንደሚሉትም የጂዳው የሰላም ውይይት ከጅምሩ ብዙ ችግሮች አሉበት። “ ውይይቱ ምንም እንኳ የሰባዊ እርዳት መታላለፊያ ለማስከፈት ያቀደ ቢሆንም የሰብዊ እርዳታ የሚሰጡና የሚያድሉ የሲቪል ማህበራት ተወካዮች ግን በስብሰባው ተስታፊዎች አልሆኑም። ይህ ደግሞ የተኩስ ማቁም ስምምነትን ብቻ ሳይሆን ለዘላቂ ሰላም አስተዋጾ ሊያደርጉ የሚችሉትን የሲቪክ፤ የሀኪሞችና ሌሎች የሙያ ማህበራትን የሚያገልና ያለፈውን ስህተት የሚደግም አስራር ነው። ሁለቱን ጀነራሎች በማደራደር የሚመጣ መረጋጋትም ሆነ ሰላም አይኖርምም በማለት ለሱዳን ሰላምና መረጋጋት ሊያመጣ የሚችለው የሲቪል አስተዳደር ብቻ ቢሆንም፤ ይህ ግን በጂዳው ውይይት አጀንዳ አልሆነም በማለት ቅሬታቸውን ጭምር ገልጸዋል።
ገበያው ንጉሴ
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሰ