1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

«የሱዳን ጦር የኢትዮጵያን ግዛት አለቀቀም» ዉሚ

ማክሰኞ፣ ጥር 25 2013

በትግራይ ክልል በዘጠና ሁለት የእርዳታ መስጫ ጣቢያዎች ሰብዓዊ ድጋፍ እየተዳረሰ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ። በሌላ በኩል የኢትዮጵያና የሱዳን የድንበር ጉዳይ አሁንም በሰላም እንዲፈታ ኢትዮጵያ ጥረት እያደረገች ቢሆንም የሱዳን ጦር ሠራዊት ግን አሁንም የኢትዮጵያን ድንበር እንደያዘ ነዉ።

Ethiopia Addis Abeba Botschafter Dina Mufti
ምስል፦ Author Solomon Muchie/DW

የኢትዮጵያ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር መግለጫ

This browser does not support the audio element.

በትግራይ ክልል በዘጠና ሁለት የእርዳታ መስጫ ጣቢያዎች ሰብዓዊ ድጋፍ እየተዳረሰ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ። ሆኖም በአንዳንድ ውስን ቦታዎችና ተፈላጊ የቀድሞው የሕወሓት አመራሮች ይኖሩባቸዋል ተብለው በሚገመቱ ሥፍራዎች ላይ የፀጥታ ጉዳይን መነሻ በማድረግ ድጋፎችን ለማድረስ እንቅፋት መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቃል። የኢትዮጵያና የሱዳን የድንበር ጉዳይ አሁንም በሰላም እንዲፈታ ኢትዮጵያ ጥረት እያደረገች ቢሆንም የሱዳን ጦር ሠራዊት ግን አሁንም የኢትዮጵያን ድንበር እንደያዘ መሆኑም ሚኒስቴሩ በሳምንታዊ መግለጫው አስታውቃል። በኮሮና ተኅዋሲ ሥጋት ምክንያት በአዲስ አበባ ይደረግ የነበረው የአፍሪቃ ሕብረት መደበኛ የመሪዎች ጉባኤ በበይነ መረብ እንዲከናወን ውሳኔ ላይ መደረሱም ተገልጿል።

ሰለሞን ሙጬ 

አዜብ ታደሰ 

ማንተጋፍቶት ስለሺ 
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW