1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሲቪክ ድርጅቶች ምክረ ሀሳብ - ለተመድ

ዓርብ፣ መጋቢት 20 2016

25 ሀገር በቀል የሲቪል ማህበራት የተበበሩት መንግሥታት በየ አራት ዓመት ተኩል የሁሉንም አባል ሀገራት የሰብዓዊ መብት ሁኔታ ለመከታተል በሚያዘጋጀው ሁለንተናዊ ወቅታዊ ግምገማ መንግሥት ከሚያቀርበው ግምገማ በተጓዳኝ በ12 የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የራሳቸውን ትይዩ ዘገባ በጋራ አዘጋጅተው ዛሬ ውይይት አድርገውበታል

የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የተመድ የሰብአዊ መብቶች መርህን በዘከረበት ወቅት (ፎቶ ከክምችታችን)
የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የተመድ የሰብአዊ መብቶች መርህን 75ኛ ዓመት በዘከረበት ወቅት (ፎቶ ከክምችታችን)ምስል Hanna Demssie/DW

የሲቪክ ድርጅቶች ምክረ ሀሳብ - ለተመድ

This browser does not support the audio element.

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሥለ ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ሁኔታ ያለዉ ግምገማ፤ የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ እንዲሆን የሲቪል ማሕበራት ጠየቁ።25 የኢትዮጵያ የሲቪል ማሕበራት ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሚያቀርቡት ትይዩ ዘገባ  እንዳሉት የድርጅቱ ግምገማ በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ላይ እንዲመሰረት ጠይቀዋል።የሲቪል ማህበረሰባቱ ድርጅቶች ገለልተኛ እና አማራጭ ጉዳዮችን በማቅረብ የሰብአዊ መብት ሁኔታ እንዲሻሻል ከጠየቁባቸው ጉዳዮች መካከል የወንጀል ፍትሕ ሥርዓት፣ የማረሚያ ቤት ሁኔታዎች፣ የሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ፣ የተፈናቃይ መብቶች፣ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት ይገኙባቸዋል።ሰለሞን ሙጬ ከአዲስ አበባ

የተመድ ሁለንተናዊ ወቅታዊ የሰብአዊ መብቶች ግምገማ

25 ሀገር በቀል የሲቪል ማህበራት የተበበሩት መንግሥታት በየ አራት ዓመት ተኩል የሁሉንም አባል ሀገራት የሰብዓዊ መብት ሁኔታ ለመከታተል በሚያዘጋጀው ሁለንተናዊ ወቅታዊ ግምገማ መንግሥት ከሚያቀርበው ግምገማ በተጓዳኝ በ12 የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የራሳቸውን ትይዩ ዘገባ በጋራ አዘጋጅተው ዛሬ ውይይት አድርገውበታል።

የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት የሁሉም የተመድ አባል ሀገራት የሰብአዊ መብት መዛግብትን ለመገምገም በሚጠቀመው በዚህ ልዩ ዘዴ ፣ ሀገራት የሰብአዊ መብት ሁኔታቸውን ለማሻሻል ምን አይነት እርምጃ እንደወሰዱ እንዲገልጹ እድል ይሰጣል። ሲቪክ ድርጅቶቹ ይህንን የሚያቀርቡት የተባበሩት መንግሥታት ከሚሰጠው ግምገማ እና ምክረ ሀሳብ በፊት "የራሳችንን ችግር ራሳችን መፍታት ይኖርብናል" በሚል መነሻ መሆኑን ከ 25 ተቋማት አንዱ የሆነው የቪዥን ኢትዮጵያ ፎር ዴሞክራሲ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ታደለ ደርሰህ ነግረውናል።

ድርጅቶቹ ምን ምን ጉዳዮች ላይ ትኩረት ይሰጥ አሉ ?

ድርጅቶቹ ባቀረቡት ትይዩ ዘገባ የተባበሩት መንግሥታት በተለይ በወንጀል ፍትሕ ሥርዓት፣ በማረሚያ ቤት ሁኔታዎች፣ በሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ፣ የተፈናቃይ መብቶች፣ ሐሳብን በነፃነት በመግለጽ መብቶች፣ በሕፃናት መብት፣ በአካል ጉዳተኞች መብቶች ላይ የሚሰጣቸው ምክረ ሀሳቦች ላይ ነባራዊ እውነታዎችን ያገናዘበ እንዱሆን አመልክተዋል። ለችግር ተጋላጭ የሆኑ ሕዝቦች ድምጽ እንዲሰማ እና በኢትዮጵያ የሚስተዋሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ለመፍታት ተጨባጭ ርምጃዎች መወሰድ እንዳለባቸውም አቋማቸውን ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ከዚሕ ቀደም የተደረጉትንም ሆነ ያሁኑን የመብት ይዞታ ዘገባ ይከታተላልምስል Ethiopian Human Rights Commission

ይህንን አሰራር ተከትሎ የተባበሩት መንግሥታት የሚሰጠውን ምክረ ሀሳብ እንከታተላለን ያለው ብሔራዊው የሰብዓዊ መብት ድርጅት - የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ባለፉት ሁለት እና ሦስት ዓመታት ይህንን ጉዳይ ሲከታተል መቆየቱን የዋና ኮሚሽነር ጽ/ቤ ኃላፊ  አልባብ ተስፋዬ ገልፀዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ሁለንተናዊ ወቅታዊ የሰብአዊ መብቶች ግምገማ የ193ቱን የተባበሩት መንግሥታት አባል ሀገራት የሰብአዊ መብት መዛግብትን የሚገመግም ሂደት ነው። 3ኛው ሁለንተናዊ ወቅታዊ የሰብአዊ መብቶች ግምገማ ዑደት በኢትዮጵያ ሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ ላይ ያተኮረ የነበረ ሲሆን አራተኛው ዙር በዚህ ዓመት መገባደጃ ላይ ይከናወናል።

ሰለሞን ሙጬ

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW