1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የሲዳማዉ ጥፋት

ረቡዕ፣ ሐምሌ 24 2011

ፖሊስ ሥለሞቱት ሰዎች ቁጥር የሚያዉቀዉ ሆስፒታል ደርሰዉ ስለሞቱት ወይም አስከሬናቸዉ ሆስፒታል ስለደረሰ ሟቾች ብቻ ነዉ።በየአካባቢዉ ተገድለዉ የተቀበሩ ሰዎች በፖሊስ ስሌት ዉስጥ አለመካተታቸዉን አዛዡ አስታዉቀዋል

Hawassa - Polizei-Vizekommandeur
ምስል፦ DW/S. Wogayehu

በሲዳማዉ ረብሻ ከ50 በላይ ሰዎች ተገደለ

This browser does not support the audio element.

ካለፈዉ ኃምሌ 11 ጀምሮ የሲዳማ ዞንን ባመሰቃቀለዉ ግጭትና ረብሻ በትንሹ 53 ሰዎች መገደላቸዉን የዞኑ ፖሊስ አዛዥ አረጋገጡ።ምክትል ኮማንደር ዳኛቸዉ ደምሴ ዛሬ እንዳስታወቁት ፖሊስ ሥለሞቱት ሰዎች ቁጥር የሚያዉቀዉ ሆስፒታል ደርሰዉ ስለሞቱት ወይም አስከሬናቸዉ ሆስፒታል ስለደረሰ ሟቾች ብቻ ነዉ።በየአካባቢዉ ተገድለዉ የተቀበሩ ሰዎች በፖሊስ ስሌት ዉስጥ አለመካተታቸዉን አዛዡ አስታዉቀዋል።ከሟቾቹ በተጨማሪ 54 ሰዎች መቁሰላቸዉን የፖሊስ አዛዡ አስታዉቀዉ፣  በረብሻዉ የተጠረጠሩ 935 ሰዎች መያዛቸዉን አረጋግጠዋል።በረብሻዉ ፋብሪካዎች፣ የሸቀጥ መደብሮች፣ ሆቴሎች፣ መኖሪያና መስሪያ ቤቶች መዉደማቸዉን፣ ገሚሶቹ መዘረፋቸዉንም ፖሊስ አስታዉቋል።

ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ

ነጋሽ መሐመድ

እሸቴ በቀለ
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW