1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሲዳማ ክልል በአራት የዞን አስተደደራዊ መዋቅሮች ሊደራጅ ነው

ቅዳሜ፣ ነሐሴ 21 2014

በሀዋሳ ከተማ መደበኛ ጉባዔውን ያካሄደው የክልሉ ምክር ቤት በክልሉ የዞን መዋቅሮችን ለማደራጀት የሚያስችለውን አዋጅ ዛሬ አጽድቋል፡፡ ዶቼ ቬለ በዞን መዋቅር ዙሪያ አስተያየታቸውን የጠየቃቸው የክልሉ ምክር ቤት አባላት አዋጁን በበጎ እንደሚመለከቱት ቢገልጹም የክልሉ ተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች ግን አፈጻጸሙ ጥንቃቄ ያሻዋል ይላሉ።

Äthiopien | Sidama region Council
ምስል Shewangizaw Wegayehu/DW

የሲዳማ ክልል በአራት የዞን አስተዳደሮች ሊዋቀር ነው

This browser does not support the audio element.

በሀዋሳ ከተማ መደበኛ ጉባዔውን ያካሄደው የክልሉ ምክር ቤት በክልሉ የዞን መዋቅሮችን ለማደራጀት የሚያስችለውን አዋጅ ዛሬ አጽድቋል፡፡ ዶቼ ቬለ በዞን መዋቅር ዙሪያ አስተያየታቸውን የጠየቃቸው የክልሉ ምክር ቤት አባላት አዋጁን በበጎ እንደሚመለከቱት ቢገልጹም የክልሉ ተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች ግን አፈጻጸሙ ጥንቃቄ ያሻዋል ይላሉ።

የክልሉ ምክር ቤት ባካሄደው ጉባዔ በክልሉ ዞናዊ የአስተዳደር እርከኖችን ለማቋቋም የወጣውን አዋጅ አጽድቋል፡፡ ዛሬ በጉባኤው የፀደቀው አዋጅ ክልሉ በአራት የዞን አስተደደራዊ መዋቅሮች እንዲደራጅ የሚያስችል ነው፡፡ በአዋጁ መሠረት የሚደራጁት ዞኖች ሰሜናዊ ፣ ደቡባዊ  ፣ ማዕከላዊና ምሥራቃዊ ሲዳማ ዞን በሚል የተሰየሙ መሆናቸው ተመልክቷል፡፡
የሚዋቀሩት ዞኖች የክልሉን የሕዝብ አሠፋፈር ፣ የመልካምድር አቀማመጥና ለልማትና ለመልካም አስተዳደር ያላቸውን ጠቀሜታ መሠረተ በማድረግ በተካሄደ ጥናት የተለዩ መሆናቸው በጉባኤው ላይ  ተገልጿል፡፡
የም/ቤቱ አባላት የዞን መስተዳድር መዋቅር የክልሉን መስተዳድር ከወረዳዎች ጋር የሚያገናኝ አስተዳደራዊ እርከን በመትከል የሕዝብ ተደራሽነት እንዲኖረው ያስችላል የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል ፡፡
ዶቼ ቬለ DW ያነጋገራቸው የክልሉ ዋነኛ ተፎካካሪ ፖርቲ የሆነው የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ሲአን ዋና ፀሐፊ አቶ ለገሰ ላንቃሞ የመዋቅሩ መዘርጋት መልካም ቢሆንም  አፈጻጸሙ ላይ ግን ጥንቃቄ ያሻዋል ይላሉ፡፡  ክልሉ ከተመሠረተ ሁለት ዓመታት ቢያስቆጥርም እስከአሁን የዞን መዋቅር አልተዘረጋም ፣ እኛም ይህ እንዲሆን ስንጠይቅ ቆይተናል ያሉት አቶ ለገሠ ‹‹ ይሁንእንጂ የየዞኖቹ ማዕከላት እንግልት እንዳይፍጥሩ አማካኝ ሥፍራ ሊሆኑ ይገባል ፡፡ በዞን መዋቅር ውስጥ የሚካሄዱ ሹመቶችና የባለሙያ ቅጥሮች ከጎሳ ትስስርና ከመጠቃቀም በጸዳ መልኩ በብቃት ብቻ እንዲሆኑ ጥንቃቄ መደረግ ይኖርበታል ›› ብለዋል፡፡ ትናንት የተጀመረው የሲዳማ ክልል ም/ቤት ቀደም ሲል በርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ የቀረበውን የ2014 ዓ.ም. የሥራ አፈጻጸም ክንውን አዳምጧል፡፡

ሸዋንግዛው ወጋየሁ
እሸቴ በቀለ 
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW