የሳህል ግዛቶች ህብረት፤ አንድነት ወይስ እኩል ያልሆነ አጋርነት?
ቅዳሜ፣ መስከረም 10 2018
የሳህል ግዛቶች ህብረት፤ አንድነት ወይስ እኩል ያልሆነ አጋርነት?
የማሊ፣ ኒጀር እና የቡርኪናፋሶ መንግሥታ በወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ከተገረሱ በኋላ ከሁለት ዓመታት በፊት የተመሰረተዉ የሳህል ግዛቶች ህብረት (AES) በያዘዉ ያልተሟሉ ግቦች እና የኢኮኖሚ ተስፋዎች ብሎም ሚዛናዊ ያልሆኑ ጥቅሞች በማሊ፣ ኒጀር እና ቡርኪናፋሶ ትችቶች ገጥሞታል። ታዲያ የሳህል ግዛቶች ህብረት ዛሬ እስከ ምን ድርሶ ይሆን?
በጎርጎረሳዉያኑ መስከረም ወር 2023 ማሊ፣ ቡርኪናፋሶ እና ኒጀር የሳህል መንግስታት ጥምረትን (AES)ን ሲመሰርቱ በወታደራዊ ጁንታ በሚመሩት ሀገራት መካከል እንደ ወታደራዊ መከላከያ ስምምነት የተፀነሰ እና የጂሃዲስት ቡድኖችን ለመዋጋት እና ብሔራዊ ሉዓላዊነትን ለማስከበር ነበር። ቆየት ብሎ ግን ህብረቱ ምኞቱን በማስፋት ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ውህደትንም አካቷል።
የሳህል ግዛቶች ህብረት ከተመሰረተ ከሁለት ዓመታት በኋላ ህብረቱ ያደርገዋል በተባለዉ እና በተጠበቀው ብሎም ባለዉ እውነታ መካከል ያለው ልዩነት ሰፊ መስሎ ታይቷል። የህብረቱ የኤኮኖሚ ሁኔታ ደካማ እና ለብዙ ዜጎች የዕለት ተዕለት ኑሮ ብዙ መሻሻልን ያላሳየ፤ ምናልባትም የሳህል ግዛቶች ህብረት የተባባሰ የጸጥታ ችግር እያጋጠመው ነው። የፀጥታ ችግሩ በተለይም በማሊ እና ቡርኪናፋሶ ሰፊ የሆኑ የገጠር ክፍሎች ዛሬ ከመንግስት ቁጥጥር ውጭ መሆናቸዉ ነዉ። በኒጀር ይፋዊ መሻሻል እንዳለ ቢነገርም ሁኔታዉ አሁንም አሳሳቢ ሆኖ እንደቀጠለ ነዉ።
ኒጀር፡ በስትራተጂያዊ ድጋፍ እና በፖለቲካ መገለል መካከል
ስለ ሳህል መንግስታት ህብረት ያለው ጥርጣሬ በተለይ በኒጀር በጣም ጠንካራ ሆኖ ይታያል። በኒጀር የወጣቶች ንቅናቄ መሪ የሆነዉ እንደ ሲራጂ ኢሳ ያሉ ተቺዎች፣ መንግሥት ከህብረቱ በምላሽ ከሚያገኘው ትርፍ ይልቅ ለሳህል ግዛቶች ህብረት የበለጠ መዋዕለ ንዋይ ያፈሳል ባይናቸዉ። ሲራጂ ኢሳ እንደሚሉት ከሆነ "ህብረቱ ከተመሰረተ ጀምሮ ኒጀር በቁልቁለት መንገድ ላይ ትገኛለች"።
"የምናመርተዉን ዘይት ለማሊ እና ለቡርኪናፋሶ ሀገር ውስጥ ከምንሸጠዉ ዋጋ በግማሽ ቀንሰን እንሸጣለን። ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታችንን ስናቋርጥ ወይም መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ስናባርር ከሳህል መንግስታት ህብረት «AES» አጋሮቻችን ጋር ግን እንደተለመደው መስራታቸውን ቀጥለዋል።" ሲል ተናግሯል።
ከዚህ በተጨማሪ ይላል ሲራጂ ኢሳ ከዚህ በተጨማሪ፡ "የኒጀር ወታደሮች የማሊን ወይም የቡርኪናፋሶን ግዛት በተደጋጋሚ ሲከላከሉ ቆይተዋል፤ ነገርግን ከእነዚህ ሀገራት በአንጻሩ ምንም የተደረገ ነገር የለም።" በሌላ በኩል
ስለ ሳህል መንግስታት ህብረት ብሩህ አመለካከት ያላቸዉም አሉ። ተፅኖ ፈጣሪዉ ሙሳ አዳሙ የሳህል መንግስታት ህብረት የኒጀርን ጂኦፖለቲካዊ አቋም ያጠናክራል የሚል እምነት አላቸዉ።
የምዕራብ አፍሪቃ የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ «ECOWAS» ቀውስ ዉስጥ በነበረበት እና የቤኒን ድንበር ተዘግቶ በነበረበት ወቅት ቡርኪናፋሶ ክልላዊ የሎጂስቲክስ ድጋፍ ስታደርግ፤ ኒጀር በፀረ ሽብር ትግል ሁለት ቁርጠኛ አጋሮችን አግኝታለች፤ ሲሉም ለDW ተናግሯል።
ማሊ፡- ኢኮኖሚያዊ ውህደት አሁንም አስቸጋሪ ነው።
በማሊውስጥ የሚሰሙት ትችቶች በይበልጥ በኢኮኖሚ እድገት ላይ ያተኮረ በፀጥታ ትብብር ጉዳይ ላይ ደግሞ የቀነሰ ነዉ። በባማኮ ማዕከላዊ ገበያ፣ እንደ ሞዲቦ ቦይሬ ያሉ ነጋዴዎች በሽያጭ መቀነስ እና አነስተኛ ትርፋማነት ላይ ያማርራሉ። ብዙዎች የጋራ ገበያን እና የጋራ መገበያያ የሆነዉን « CFA franc» ን መሰረዝን ጨምሮ ጥልቅ ኢኮኖሚያዊ ውህደትን ይፈልጋሉ። ሉዓላዊ መገበያያ ገንዘብ እንያዝ የሚለዉ የረጅም ጊዜ ክርክር ዳግም እየተጠናከረ ነው።
እንደ ኢቦው ሳይ ያሉ ተፅኖ ፈጣሪዎች ብሔራዊ የመገበያ ገንዘብ የዳግም ሉዓላዊነት ምልክት አድርገው ይመለከቱታል። ሆኖም እንደ ሞዲቦ ማኦ ማካሎው ያሉ ኢኮኖሚ ጉዳይ ምሁሮች ደግሞ ጥንቃቄ እንዲደረግ ያሳስባሉ። ኤኮኖሚዉ ካልተዋቀረ የሚመጣዉ ብሔራዊ መገበያያ ገንዘብ ደካማ ሆኖ ይቀጥላል ባይ ናቸዉ።
"በመሰረቱ ኢኮኖሚያችንን ካላዋቀርን አዲሱ ምንዛሪ ደካማ ይሆናል" ሲሉ የኤኮኖሚ ምሁሩ ለዴቼ ቬለ ተናግረዋል። ቡርኪናፋሶ፡ የማያቋርጥ ብጥብጥ እና በወታደራዊ ስልት ላይ የሚደርሰዉ ትችት
ለቡርኪናፋሶ ህዝብ የሃገሪቱ የፀጥታ ሁኔታ ዋነኛ ጉዳዩ ነዉ። በግንቦት 2025 ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት አለው የሚባለዉ JNIM (ጀማአት ናስር አል እስላም ዋል-ሙስሊሚን) የተሰኘዉ ጀሃዲስት ቡድን በቡርኪናፋሶ ሰሜናዊ የጂቦ ከተማ ወታደሮችን እና ሲቪሎችን ጨምሮ ከ100 በላይ ሰዎችን ሲገድል ከፍተኛዉ ደረጃ ላይ ደርሷል።
በኢብራሂም ትራኦሬ የሚመራው ወታደራዊ መንግስት ባልሰለጠኑ የአካባቢ ሚሊሻዎች እና ወታደራዊ ቀዉስ ላይ እንደሚተማመን ታዛቢዎች ይናገራሉ። ይሁንና አንዳንድ ተንታኞች የሳህል ግዛቶችህብረት « AES » ከተመሠረተ ወዲህ በቡርኪናፋሶ ትንሽም ቢሆን ተጨባጭ መሻሻል ታይቷል ብለው ያምናሉ።
ደህንነት፡ የጋራ ሃይል ህልም ሆኖ ይቀራል
የሳህል ግዛቶች ህብረት «የ AES » ቁልፍ ቃል ኪዳን ከሆነዉ መካከል አንዱ የጋራ ወታደራዊ ኃይልን ማቋቋም ነበር። ከሁለት ዓመት በፊት ቃል ተገብቶ በወረቀት ላይ የሰፈረዉ ነገር ዛሬም ወረቀት ላይ ብቻ እንዳለ ነዉ። የኒጀር የሰብአዊ መብት ተሟጋች አልሃጂ ባባ አልማኪያ ይህንን እንደ አንድ ከባድ ውድቀት ይቆጥሩታል።
"የ «AES» ጥምር ኃይል ቢሰራ ኖሮ የፀጥታው ሁኔታ ዛሬ በጣም የተለየ ይሆን ነበር። ይልቁንም በግንባር ከሚገኙት በጣም ጥቂት መኮንኖች በቀር ከጠረጴዛ ጀርባ ስለሚገኙ ብዙ መኮንኖች ነዉ የምንሰማዉ።
መብት ተሟጋቼ አልሃጂ ባባ አልማኪያ፤ መንግስታት ወታደራዊ ኃይልን በሙሉነት አቋቁመው ሽብርተኝነትን ለመዋጋት በብቃት ሊጠቀሙበት ይገባል።"
አንቶንዮ ካሽካሽ / አዜብ ታደሰ
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሔር