የሳውዲ የምህረት አዋጅ መገባደድና የነዋሪው ስጋት
ሐሙስ፣ ጥቅምት 14 2006ማስታወቂያ
በቀጣዩ ሳምንት ጥቅምት 24 ቀን 2006 ዓም ተግባራዊ ይደረጋል። በርካታ እድሉን መጠቀም የሚችሉ ሕገወጥ የነበሩ ነዋሪዎችን ጨምሮ፤ ሕጋዊ ቪዛ ይዘው ከአሰሪያቸው ውጭ በነጻነት ይሰሩ የነበሩ ጉዳያቸዉን ለማሳካት ላይ ታች ቢሉም እስካሁን ብዙዎች እንዳላጠናቀቁ ይነገራል። ከደላሎች እስከ ሃገራቸው ቆንስልና ኤምባሲ ተወካዮች፣ ከግል ቪዛ ሻጭ ሳውዲ አሰሪዎች፣ ከፊል ተወካዮች እስከ ሳውዲ መንግስት መሥሪያ ቤቶች በተወሳሰበ አሠራር ውስጥ ተዘፍቀው ጉዳያቸው ከዳር ያልደረሰዉም ቁጥር ቀላል ነው አይባልም። የተራዘመዉ የጊዜ ገደብ እየተገባደደ ባለበት በዚህ ወቅት የሳውዲ መንግስት አስፈላጊዉን አከናዉነዉ ሕጋዊ መኖሪያ ፍቃድ ያልተቀበሉትንም ሆነ ያስጠጓቸዉን እንደሚቀጣ እያስጠነቀቀ ነዉ። ብዙዎች በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ መስሪያ ቤት አስፈላጊውን አገልግሎት በአፋጣኝ አልሰጠንም በማለት እንደሚያማርሩ እና ስጋት እንደገባቸው የጅዳዉ ወኪላችን ነብዩ ሲራክ በዘገባዉ ገልጿል።
ነብዩ ሲራክ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሂሩት መለሠ