የሳዑዲ ድንበር ጠባቂዎች ኢትዮጵያዉያንን ገደሉ
ረቡዕ፣ ነሐሴ 17 2015
የሳዑዲ አረቢያ ጦር ኃይል ከየመን ወደ ሳዑዲ አረቢያ ለመግባት የሞከሩ በብዙ መቶ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን ስደተኞችን በጥይት ደብድቦ መግደሉን ሁዩማን ራይትስ ዋች አጋለጠ።ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት እንደሚለዉ የሳዑዲ አረቢያ ወታደሮች ጥይታቸዉን በስደተኞቹ ላይ «እንደ ዝናብ አዉርደዉታል።»
የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም የሳዑዲ አረቢያ ወታደሮች በየመን በኩል አቋርጠዉ ሳዑዲ አረቢያ ለመግባት የሚሞክሩ ስደተኞችን በተለያየ ጊዜ መግደላቸዉን አረጋግጧል።የሳዑዲ አረቢያ መንግስት ግን ወቀሳዉን አልተቀበለዉም።
የታጠቁ የሳውዲ አረቢያ ጠባቂ ወታደሮች፣በየመን በኩል አድርገው በእግራቸው በአሁኑ ሰዓት ውደ ግዛታቸው ለማለፍ በሚሞክሩት የኢትዮጵያ ስደተኞች ላይ „…ጥይታቸው እንደ ዝናብ በእነሱ ላይ አርከፍክፈው በብዙ መቶ የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት አጥፍተዋል።»
የኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሰቆቃ በሳዑዲ እስር ቤቶች
ይህን የሚለው እዚህ ትላንት የወጣው ለሰበዓዊ መብት መከበር በዓለም ዙሪያ በአሁኑ ጊዜ የሚሟገተው «HRW የተባለው ድርጅት ነው፡፡ አውሮጳ የተበተነው ሰነድ ረዥም ነው፡፡ከ70 ገጾች በላይ ይዞአል፡፡
በፊልምና በድምጽ ፣በበርካታ ማሽረጃችም ተደግፎ ፣ለሰበኣዊ መብት መከበር በዓለም ዙሪያ የሚሟገተው HRW የሚባለው ድርጅት „ በብዙ መቶ የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ስደተኞን፣ሕጻናት ልጆችን እና እናቶችን ጭምር በጅምላ ድንበሩ ላይ በጥይትና በፈንጂ ቦንብ ገድሎአቸዋል“ ብሎ የሳውዲን መንግሥት ከሶአል፡፡
„መሠረት የሌለው የፈጠራ ክስ ነው „ ብሎም የሳውዲ መንግሥት አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው „…ክሱን በበኩሉ ውድቅ አድርጎት ለማለፍ ሞክሮአል፡፡“
„በእኛ እምነት ሚሰተር ሳም ዱበርሊ- የድርጅቱ ተጠሪ በጀርመን አገር ለጣቢያችን ለ ዲ ደብልዩ እንደ አሉት - „በእኛ እምነት፣ በድምበሩ ላይ በአለፉት ጊዜያት የሰበሰብናቸው መረጃዎች፣እንዲሁም የዓይን ምስክሮች እንደሚያረጋግጡት፣ከባድ መሣሪያ የታጠቁት የሳውዲ ወታደሮች ለስደተኞቹ ሕይወት መጥፋትና እነሱ ተጠያቂዎች እንደሆኑ በቂ ማሥረጃዎች በእጃችን ላይ አሉን „ ብለዋል፡፡
ሳውዲ ውስጥ በሚኖሩትና የቤት ሠራተኞ እና በሌሎቹም የኢትዮጵያ ዜጎች ላይ ላይ እዚያ የሚፈጸመው በደልና ጥቃት ግዲያም ጭምር - ተመልካቾች እዚህ እንደሚሉት - አዲስ ነገር እንደአልሆነ ይታወቃል፡፡
„ልዩ የሚያደርገው ሚሰተር ሳም ዱበርሊ -ተጠሪው- እሳቸው ለጣቢያችን አያይዘው እንደ አሉት „አንድ ነገር ነው፡፡“
„ እኛ በየመንና በሳውዲ ድንበር ላይ የሚካሄዱትን ማንኛውንም ነገሮች፣እስከ ግድያ ድረስ ለአለፉት ስምንትና ዘጠኝ አመታት በቁራኛ ዓይን ስንከታተለውና ስንዘግበው ቆይተናል፡፡ ይህኛው ህን በመጠኑና በስፋቱ እንዲሁም በሟቾቹ ቁጥርም፣በአገዳደሉም ጭቃኔ፣ከአለፉት አመታት እጅግ የከፋና የተለየ ነው“ ብለዋል፡፡
„ሳውዲንና እና የመንን የሚያዋሰወነው ድንበር ሰው የማይደርስበት ድንጋያማ በረሃ በመሆኑ፣ለምን የድንበር ጠባቂዎቹ እንደዚህ ዓይነቱን ግድያና ግፍ እዚያ በስደተኞቹ ላይ እንደፈጸሙ መልስ መስጠት ያለበት ክፍል ቢኖር „ ተጠሪው እዚህ እንዳሉት“ የሳውዲ መንግሥት ብቻ ነው፡፡“
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ነጋሽ መሐመድ
ማንተጋፍቶት ስለሺ