የሴኔጋል ምርጫና ዉጤቱ
ረቡዕ፣ የካቲት 21 1999ማስታወቂያ
ምርጫዉ በተካሄደ እለት የፕሪዝደንት አብዱላዬ ዋድ ደጋፊዎች የምርጫዉ አሸናፊ ሆነናል በማለት ደስታቸዉን ሲገልጹ ታይተዋል። በትናንትናዉ እለት በታተሙ የአገሪቷ ጋዜጦችም ዋዴ ማሸነፋቸዉን የሚገልጽ ዘገባም አዉጥተዋል፣ ነገር ግን የፕሪዝደንት ዋድ ተቀናቃኞች ዉጤቱ ተጭበርብሯል ሲሉ ቅሪታቸዉን ማሰማታቸዉን ቀጥለዋል። በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር የAfrica Press Agency ጋዜጠኛን አዜብ ታደሰ በስልክ አነጋግራ ነበር ።