የስሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ጉባኤ ፍፃሜና ውጤቱ
ሐሙስ፣ ሰኔ 19 2017
የስሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት ኔቶ የመሪዎችየሁለት ቀን ጉባኤ ባለ አምስት ነጥብ የጋራ የመክላክያ ሰነድ በማውጣት በስኬት የተጠናቀቀ መሆኑ ተገልጿል። ባለፉት ሁለት ቀናት በነዘርላንድስ ዘሄግ የተክሄደው ጉባኤው ያአሜሪካውን መሪ ፕሬዝዳንት ትራምፕን ጨምሮ የ32 አባል አገራት መሪዎችና የተጋበዙ እንግዶች የተገኙበት ነበር።
የዚህ አመቱ ጉባኤ ለምን ልዩና ተጠባቂ ሆነ?
የሁለተኛ የዓለም ጦርነትን ማብቃት ተክትሎ እ ኣ አ በ1949 አም በአሜሪካ ፊታውራሪነት በያኔዋ ሶቭየት ህብረት አንጻር የተቋቋመው ግዙፉ የጦር ሀይል፤ ፒረዝዳንት ትራምፕ ለመጀመሪያ ግዜ ወደ ስልጣን እስከመጡበት ግዜ ድረስ ቢያንስ ከአባላቱ ጥያቄ የሚነሳበት አልነበረም። ፕሬዝዳንት ትራም እ እ አ በ2016 ተመርጠው ወደ ስልጣን እንደመጡ ግን በኔቶ አስፈላጌትና ቀጣይነት ላይ ያነሷቸውን ጥያዎችዎች ዳግም ወድ ስልጣን ሲመጡም አጉልተው በማንሳታቸው ምክኒያት የዘንድሮው ጉባኤ ስኬት አሳሳቢ ሆኖ ነበር።
አሚሪካ ካውርፓየኔቶ አባል አገራት በተለየ ሁኔታ ለዩክሬን የምትሰጠውን እርዳታ ላትቀጥል እንደምትችል መገለጹ፣ አባል አገራት የሚጠበቅብቅባቸውን መዋጮ እስካላሟሉ ድረስ ባድርጅቱ ደንብ አንቀጽ አምስት መሰረት ክሚደርስባቸው ጥቃት ሊከላክልላቸው የሚችል ኃይል ሊኖር እንደማይችልና ከእንግዲህም አባል አገራት ክገቢያቸው አምስት ከመቶ ለመከላከያ እንዲመድቡ መጠየቁ አባል አገራቱን እንዳይከፋፍልና ድርጅቱንም አደጋ ላይ እንዳይጥለው አስግቶ ንበር ።
ከጉባኤው የወጡ ውሳኔዎችና መግለጫዎች
ሆንም ግን ባለፉት ሁለት ቀናት በኔርላንድስ ዘሄግ የተካሄደው ጉባኤ መሰረታዊና አስፈላጊ በሆኑ አጀንዳዎች በተለይም በመከላከያ ወጭ ላይ በመስማማትና በመወሰን በስኬት የተጠናቀቀ መሆኑን የድርጅቱ ዋና ጸሃፊ ማርክ ሩተ አስታውቀዋል፤ “ የኔቶ መሪዎች በሄግ የመከላከያ እቅድ ላይ ተስማምተዋል። በዚህ ዕቅድ መሰረት አገሮች ከጠቅላላ ገቢያቸው 5 ከመቶውን ለመክለካያ ወጭና ኢንቭስትሜንት ያውላሉ። ከዚህም 3.5 ከመቶ ለጦር መሳሪያዎች ወጭ፤ 1.5 ከመቶው ለመከላክያ መሰረተ ልማት የሚውል መሆኑን አስታውቀዋል። ሚስተር ሩተ ይህ ምን ማለት እንደሆነ ሲያብራሩም “ ይህ ማለት ምንም አይነት ተግዳሮት ወይም ስጋት ከሩሲያ ይምጣ ወይም ከስሸባሪዎች ይቃጣ ፣ የሳይበር ጥቃትም ይሁን ወይም ስልታዊ ፉክክር፣ ሁሉንም በየመጡበት በብቃት ለመከላከልና በአባል አገራቱ የሚኖሩት አንድ ቢሊዮን ህዝቦች በነጻነትና በክብር እንዲኖሩ ያስቻላል ማለት እንደሆነ ገልጸዋል።
ለጉባኤው መሳክት የተደረጉ ዝግቶችና ጥንቃቄዎች
ይህ እንዲሆን የጉባኤው አዘጋጆች አጀንዳዎቹ ውስንና ከፕሬዝዳንት ትራም ጋር ውዝግብ የሚያስገቡ እንዳያሆኑ፤ እንዲሁም የጉባኤው ግዜ አጭር እንዲሆን መደረጉንና ለዚህም በተለይ ዋና ጸፊው ማርክ ሩተ ቁልፍ ሚና የተጫወቱ መሆናቸው ይነገራል። ክብርና ሙገሳ ይወዳሉ ለሚባሉት ፕሬዝዳንት ትራምፕም ሩተ ፕሬዝዳንቱ ለጉባኤው በጉዞ ላይ እንዳሉ ነበር ቤኢራን በወስዱት እርምጃና በተደረሰው የተኩስ ማቆም ስምምነት ምስጋናና አድናቆት የላኩላቸው።
ከጉባኤው የወጣው ባለ አምስት ነጥቡ የጋራ መግለጫም በዋናነት አባል ገራቱ የመክላከያ ወጫቸውን ወደ አምስት ከመቶ ለማሳደግ መወሰናቸውን ነው አጉልቶ ያወጣው። ለዩክሬን የሚሰጠውን እርዳታ በሚመለክትም ይሁን፤ የሩሲያ የጠላትነት ትርከት በጉባኤው ሰነዶች ላይ ለዝበው የቀረቡ ሲሆን ይህም ለጉባኤው በመግባባት መጠንቀቀ አስተዋኦ እንዳደረገ ነው የሚነገረው።፡
የአምስት ከመቶው የመከላከያ ወጭ ውሳኔ ተግባራዊነት አጠያያቂነት
ጉባኤው አሳክው የተባለው በሚቀጥሉት አስር አመታት የመካላከያ ውጭን ከጠቅላላ ገቢ አምስት ከመቶ የማድረስ ውሳኔ ተግባራዊነት ግን ከውዲሁ እያነጋገረ ነው። ፕሮግራሙ ታክስ መጨመርን፣ የማህበራዊና የጤና ወጭዎችን መቀነስን የሚጠይቅ በመሆኑ፤ ቀድሞ የስዊድን ጠቅላይ ሚኒስተር የነብሩት ካርል ቢልድት እንደሚሉት ይህን የስሜን አውሮፓ አገሮች ሊሟሉት ቢችሉም በደቡቦቹ ላይ ግን አስቸጋሪ ይሆናል ። ስፔን ከውዲሁ ቅድሚያ የምትሰጣቸው አገራዊ አጅንዳዎች ያሏት በመሆኑ በውሳኔው ልትገደድ እንደማትችል ማሳወቋ የታውቀ ሲሆን፤ ቤልጅየምና ስሎቫኪያም ቅሬታ ያላቸው መሆኑን አስታውቀዋል ተብሏል።
ገበያው ንጉሴ
ኂሩት መለሰ
ዮሀንስ ገብረ እግዚአብሔር