1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ትምህርት

Merga Yonas Bula
ማክሰኞ፣ ሰኔ 20 2009

የኢትዮጵያ የትምህርት ሚኒስቴር ከሚቀጥለዉ ዓመት ጀምሮ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከሚመረቁት መካከል 80 ከመቶዉን ወደ ስራ ዓለም ለማስገባት እቅድ እንዳለዉ ይፋ ማድረጉን የአገር ዉስጥ ዘገባዎች አመልክተዋል።

Karte Äthiopien englisch

MMT-Gov t Plan Promise 80p Job for Graduates - MP3-Stereo

This browser does not support the audio element.

በዚህ ዓመት ከአገሪቱ 33 የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች 100,000 ይመረቃሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ በእቅዱ መሰረት፣ ከነዚሁ መካከል 80,000ዎቹ ስራ እንደሚያገኙ ተገልጿል። እቅዱን እዉን ለማድረግ በዩኒቨርስቲዎችና በኢንዱስትሪዎች መካከል ያለዉን ትስስር ማጠናከር አስፈላጊ እንደሚሆን ይታመናል።

ይህ የመንግስት እቅድ ዉጤታማ እንዲሆን የኢትዮጵያ አሰሪዎች ፌዴሬሼን የበኩሉን አስተዋፆ እንደሚያደርግ የፈደሬሼኑ ፕሬዚዳንት አቶ ታደለ ይመር ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ ካሉት 300,000 በላይ አሰሪዎች መካከል ወደ 27,000 የሚሆኑት በአባልነት የተጠቃለሉበት ፌዴሬሼን ኃላፊ አቶ ታደለ ፣ አባላቱ የመንግስትን እቅድ ወደ ተግባር በመለወጡ ላይ እንዲተባበሩ ጥሪ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል።

በለንዳን የሚገኘዉ «ቻታም ሃዉስ» የተባለው የፖለቲካ ጥናት ተቋም የአፍሪቃ ፕሮግራም ተባባሪ ተመራማር  ጀሳን ሞስል፣ በየዓመቱ ከዩኒቨርስቲዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ቢመረቁም በሃገሪቱ ያለው የስራ እድል ካለዉ ፍላጎት ጋር እንደማይጣጣም ጠቅሰዋል። ይሁንና፣ ተመራቂዎች ሁሉ ከመንግሥት ብቻ የስራ ቦታ መጠበቅ እንደሌለባቸው ነው አቶ ታደለ ያስረዱት።

በአዲስ አበባ የመንግስት ሰራተኛ የሆኑት አቶ ሃላላ አሰፋ በአገሪቱ የስራ አጥነት ሁኔታ በጣም እየሰፋ ስለሚገኝ እቅዱ «እንደ እቅድ» ጥሩ ነዉ ይላሉ።

ዶይቼ ቬሌ ያነጋገራቸው ከመቀለ ዩኑቨርሲቲ በሜካንካል ኢንጅነርንግ ከአምስት ዓመት በፊት መመረቃቸዉን የሚናገሩት አቶ ጀማል ኡድን ሁመር በተማሩበት ሙያ ስራ ለማግኘት ሙከራ እንዳደረጉና ሳይሳካላቸው በመቅረቱ በግለሰብ ጋራጅ ተቀጥረው እንደሚሰሩ በመግለጽ መንግስት ለተመራቂዎች የያዘዉን የስራ እድል ፈጠራ እቅድ በጥርጣሬ እንደሚያዩት ገልጸዋል።

በዶይቼ ቬሌ የፌስቡክ ገጻችን ላይ አስተያየት ከሰጡን መካከል፣ አንዳንዶቹ «እቅዱ አሪፍ ሆኖ ሳለ የሚተገብረው አካል ግን የለም፣ እና ሁሌ እቅድ ማውጣት ምን ያረጋል? ትምህርት ጨሪሰው ለተቀመጡ ምን ፈጠረ? ሲሉ አጠያይቀዋል።

መንግሥት የዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎችን ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ በብዛት ወደ ስራ ዓለም ለማስገባት ስለወጠነው እቅድ ከትምህርት ሚኒስቴር ተጨማሪ ማብራርያ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

መርጋ ዮናስ

አርያም ተክሌ


 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW