1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የስደተኞችና የአዉሮጳ ኅብረት መፍትሄ

ማክሰኞ፣ ሰኔ 12 2010

የስደተኞችና የአዉሮጳ ኅብረት መፍትሄ

Niger Binnenflüchtlinge Flüchtlinge Vertriebene Nigeria
ምስል picture-alliance/dpa/A. Abodou

የዓለም የስደተኞችና የተፈናቃዮች ቀን

This browser does not support the audio element.

በያዝነዉ ክፍለዘመን እዚህ አዉሮጳ ቤልጅግ ዋና መዲና ብራስልስ ከተማ የሚታየዉ የስደተኛ ብዛት ቀላl የሚባል አይደለም። ከከተማዋ እምብርት ፈንጠር ብሎ በሚገኘዉ ዋና የባቡር ጣብያ አካባቢ ከተለያዩ ዓለም ሃገራት የመጡ ሰዎች ይታያሉ። ከተለያዩ የአፍሪቃ ሃገራት የመጡ ስደተኞች የስደተኝነት ማመልከቻቸዉን አስገብተዉ መልስን ለመቀበል ፈረንሳይ ሆነዉ ተራቸዉን ይጠብቃሉ። ሌሎች ደግሞ በረፈረንሳይ በኩል አቆራርጠዉ ወደ ብሪታንያ ለማቋረጥ ጥረት ያደርጋሉ። ወደ ብሪታንያ መዝለቅ የሚፈልጉት አብዛኞቹ ስደተኞች ወደብሪታንያ መሄድን የሚሹት ዘመድ ጓደኛ ስላላቸዉ ነዉ። አብዛኞቹ አፍሪቃዉያን ስደተኞች ወጣቶች ናቸዉ። አፍሪቃዉያን ስደተኞች ብራስልስ እንብርት ላይ በሚገኘዉ የባቡር ጣብያ አካባቢ አልያም ማክሲሚሊያን በሚባለዉ የመዝናኛ ፓርክ ዉስጥ ትናንሽ ድንኳንን ተክለዉ ማደርያ መዋላቸዉን አድርገዋል። እነዚህ ስደተኞች በሰሜን አፍሪቃ በኩል የሜዲተራንያንን ባሕር አቋርጠዉ የኦስትርያና የጀርመንን ድንበርን አቋርጠዉ ፤ አንዳንዶች እንደሚሉት ደግሞ በፈረንሳይ በኩል ቤልጂግ የገቡ ወጣት አፍሪቃዉያን ስደተኞች ናቸዉ። በሕጉ መሰረት እና አዉሮጳዉያንም በጋራ በደረሱበት ስምምነት መሰረት ስደተኞቹ ከየትም ይምጡ ከየትም ማመልከቻቸዉን ማስገባት ያለባቸዉ መጀመርያ እግራቸዉን ያሳረፉበት ሃገር  መሆን ይኖርበታል። ግን ይህን የጋራ ሕግና የጋራ ስምምነት አባል ሃገሮች ተመልካቾች በስራ ላይ ለማዋል በሆነና ባልሆነ ምክንያት ስምምነቱ አንዱም የአዉሮጳ ሃገር ላይ ተግባራዊ መሆን አልቻለም። በዚህ ምክንያት አዉሮጳዉያን ሃገራቱ በስደተኞች ጉዳይ ያልታሰበ ችግር ዉስጥ ከትዋቸዋል።   

ምስል picture-alliance/ dpa/dpaweb

ይልማ ኃይለሚካኤል / ቤርን ሪገርት

አዜብ ታደሰ  

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW