1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ሰብዓዊ መብቶችሰሜን አሜሪካ

በስደተኞች ጉዳይ የትራምፕ ርምጃና ተቃውሞው

ሸዋዬ ለገሠ Shewaye Legesse
ሰኞ፣ ሰኔ 2 2017

በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ትዕዛዝ በካሊፎርኒያ ግዛት የተካሄደው የስደተኞች አሰሳ ያስከተለው ተቃውሞ በጸጥታ አስከባሪዎች እና ሰልፈኞች መካከል ግጭት አስከትሏል።

የሎስ አንጀለሱ ተቃውሞ እና ፍጥጫ
የሎስ አንጀለሱ ተቃውሞ እና ፍጥጫ ምስል፦ Ethan Swope/AP/picture alliance

በስደተኞች ጉዳይ የትራምፕ እርምጃና ተቃውሞው

This browser does not support the audio element.

 

 

በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ትዕዛዝ በካሊፎርኒያ ግዛት የተካሄደው የስደተኞች አሰሳ ያስከተለው ተቃውሞ በጸጥታ አስከባሪዎች እና ሰልፈኞች መካከል ግጭት አስከትሏል። ፕሬዝደንቱ ከበርካታ አስርት ዓመታት በፊት የጥቁሮችን መብት ለማስከበር ፌደራል መንግሥት የወሰደውን ብሔራዊ ዘብን ያሰማሩበት እርምጃ ከካሊፎርንያ ግዛት ክስ አስከትሏል። ሎስ አንጀለስ ከተማ ላይ የአሜሪካ የኢሚግሩሽንና የጉምሩክ ፖሊሶች ከዓርብ ጀምረው ሕገወጥ ስደተኞች ይገኙባቸዋል ተብለው በሚገመቱ የተለያዩ የንግድ ስፍራዎች ፍተሻ ማካሄዳቸው በአብዛኛው በስደተኛ ነዋሪዎች ብዛት የሚታወቁትን የሎስ አንጀለስና አካባቢውን ከተሞች ነዋሪዎች አስቆጥቷል። ሁኔታው በምን ደረጃ ላይ ይገኛል፤ በቀጣይስ ወዴት ያመራል? የመገናኛ ብዙሃን መነጋገሪያ ሆኗል። ከዋሽንግተን ዲሲ አበበ ፈለቀን በጉዳዩ ላይ በአጭሩ በስልክ አነጋግሬዋለሁ። 

አበበ ፈለቀ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ

 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW