1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የስደተኞች እልቂት በየመን የባህር ዳርቻ

ሰኞ፣ መጋቢት 1 2006

ትናንት ምሽትም 45 አፍሪቃውያን ስደተኞች በየመን የባህር ዳርቻ መስጠማቸውን የሃገሪቱ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል ። የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ድረ ገፅ እንዳስነበበው በባህር ዳርቻዋ ከተማ በቢር አሊ ከተማ ከደረሰው ከዚሁ አደጋ 30 ሰዎችን በህይወት ማትረፍ ተችሏል ።

Reporter ohne Grenzen Fotos für die Pressefreiheit 2010
ምስል Alixandra Fazzina


ወደ ሃብታሞቹ የአረብ ሃገራት መሻገሪያ ሆና ወደ ምትታየው የመን ለባህር ጉዞ በማይመጥኑ አነስተኛ ጀልባዎች የሚያቀኑ ስደተኞች የባህር ሲሳይ መሆናቸው ተደጋግሞ ይሰማል ። ትናንት ምሽትም 42 አፍሪቃውያን ስደተኞች በየመን የባህር ዳርቻ መስጠማቸውን የሃገሪቱ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል ። የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ድረ ገፅ እንዳስነበበው በባህር ዳርቻዋ ከተማ በቢር አሊ ከተማ ከደረሰው ከዚሁ አደጋ 30 ሰዎችን በህይወት ማትረፍ ተችሏል ። ዓለም ዓቀፉ የስደት ጉዳይ ድርጅት እንዳስታወቀው ባለፈው የጎርጎሮሳውያኑ 2013 ዓም ባህር ተሻግረው ወይም ደግሞ በረሃ አቋርጠው የመን ለመድረስ ከሞከሩ ስደተኞች መካከል ከ7 ሺህ በላይ የሚሆኑት ህይወት አልፏል ። ይህም እስከዛሬ በዚህ መንገድ ከሞቱት ስደተኞች እጅግ ከፍተኛው አሃዝ ነው ። ከመካከላቸው የአፍሪቃውያኑ ቁጥር ከ2 ሺህ እስከ 5 ሺህ ይገመታል ። ተክሌ የኋላ ስደተኞች የመን ለመድረስ ስለሚከተሉት አደገኛ የባህርና የበረሃ ጉዞ የየመኑን ወኪላችንን ግሩም ተክለ ሃይማኖትን በስልክ አነጋግሮታል ።

ግሩም ተክለ ሃይማኖት

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW