የስደተኞች ከፍተኛ ችግር በበሊቢያ
ሐሙስ፣ መጋቢት 26 2011ማስታወቂያ
ሳባ ተብሎ የሚጠራዉ ሊቢያ ዉስጥ በሚገኝ የስደተኞች እና የተገን ጠያቂዎች ማቆያ ማዕከል ቁጥራቸዉ ከ 300 በላይ የሚደርሱ ስደተኞች እና ተገን ጠያቂዎች በጣም በተጣበበ ቦታ እንደሚኖሩና እጅግ አስደንጋጭ በሆነ በተመጣጠነ የምግብ እጥረት ላይ እንደሚገኙ ተገለፀ። ስደተኞቹ በከፍተኛ ጤና ችግር ላይ ይገኛሉ፤ ጉዳዩ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ነዉ ያለዉ ድንበር የለሹ የሐኪሞች ቡድን «MSF» በማቆያ ጣብያዎች በከፍተኛ የሰብዓዊ ችግር ዉስጥ በተለይ እድሜያቸዉ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ሕጻናት በማዕከሉ ውስጥ እንዲኖሩ መገደዳቸው እንዲቀር ሲል ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጥሪዉን አቅርቦአል። የዓለምአቀፉ የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን «UNHCR» በሊቢያ ያለዉ የስደተኞች አልያም የተገን ጠያቂዎች መጠለያ እንዲዘጋ ተደጋጋሚ ጥሪ ሲያደርግ እንደነበር ድንበር የለሹ የሐኪሞች ቡድን አስታዉቋል።
ሃይማኖት ጥሩነህ
አዜብ ታደሰ
ኂሩት መለሠ