የስጳኝ እና የካታላን ውዝግብ
ረቡዕ፣ መስከረም 24 2010ማስታወቂያ
በሕገ መንግሥቱን የሚጥስ ነው በሚል እንዳይደረግ የተከለከለውን ሕዝበ ውሳኔ ሂደትን እንዲያከላክሉ ማዕከላዩ መንግሥት ወደ ካታላንያ በላካቸው ፖሊሶች እና በግዛቱ ህዝብ መካከል ግጭት ተፈጥሮ ወደ 800 የሚጠጉ ሰዎች ቆስለዋል። ይህን የፖሊስ ርምጃ በመቃወም ትናንት በካታላን ብዙ ህዝብ አደባባይ ወጥቶዋል። እየተካረረ የመጣውን ውጥረት ተከትሎም የሀገሪቱ ንጉሥ ፊሊፔ ሳድሳይ ትናንት ለሀገሪቱ ህዝብ ንግግር አድርገዋል።
ገበያው ንጉሤ
አርያም ተክሌ
ነጋሽ መሀመድ