የስፖርት እና ባሕል ድግስ በለንደን
ረቡዕ፣ ሐምሌ 10 2011ማስታወቂያ
ቅዳሜ እና እሁድ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያ በስፍራው ተገኝተው የተሳተፉበት ይህ የስፖርት እና የባሕል ድግስ የተለያዩ የባሕል ምግቦች፤ ጌጣ ጌጦች፣ አልባሳት መቅረባቸውን፤ ግብረ ሰናይ ድርጅቶችም በስፍራው ተገኝተው ለታዳሚው አገልግሎታቸውን መስጠታቸውንም በላከችው ዘገባ አመልክታለች። ዘጋቢያችን ያነጋገረቻቸው በስፍራው የገኙ ታዳሚዎች ስለዝግጅቱ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። እንዲህ ባለው ዝግጅትም ለመጀመሪያ ጊዜ በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ መገኘቱም ተሰምቷል።
ሃና ደምሴ
ሸዋዬ ለገሠ
አዜብ ታደሰ