1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሶማሊያ ፖለቲካዊ አለመረጋጋትና ምርጫ

ሐሙስ፣ መጋቢት 22 2014

ሶማሊያ ውስጥ በተደጋጋሚ የተራዘመው ሀገራዊ ምርጫ በተቃረበበት በአሁኑ ወቅት የአሸባሪዎች የቦንብ እና ሌሎች ጥቃቶች ብርቱ ስጋት አሳድሯል። ታጣቂዎች በምርጫው እጩዎች፤ ባልደረቦቻቸው እና የውጭ ሃገራት ወታደሮች ላይ ጥቃታቸውን አጠናክረዋል።

Somalia Angriff
ምስል Farah Abdi Warsameh/AP Photo/picture alliance

ኧል ሸባብ ጥቃቱን አጠናክሯል

This browser does not support the audio element.

ሶማሊያ ውስጥ በተደጋጋሚ የተራዘመው ሀገራዊ ምርጫ በተቃረበበት በአሁኑ ወቅት የአሸባሪዎች የቦንብ እና ሌሎች ጥቃቶች ብርቱ ስጋት አሳድሯል። ታጣቂዎች በምርጫው እጩዎች፤ ባልደረቦቻቸው እና የውጭ ሃገራት ወታደሮች ላይ ጥቃታቸውን አጠናክረዋል። የሶማሊያ መሪዎች በሀገሪቱ ሠላማዊ የሥልጣን ሽግግርን ለማሳካት የተቀናጀ ጥረት ከምን ጊዜውም በላይ አሁን ያስፈልጋል ብለዋል። በአንድ በኩል ተደጋጋሚ የሽብር ጥቃቶችን የሚሰነዝረው ኧል ሸባብ የተሰኘው የሶማሊያው ታጣቂ ቡድን ጥቃቱን አጠናክሯል። በሌላ በኩል ደግሞ የሀገሪቱ ፕሬዚደንት እና ጠቅላይ ሚንሥትር በፖለቲካ አለመግባባታቸው ተባብሷል። የዚህ ሁሉ ድምር ሶማሊያን አደጋ ላይ ጥሏል ሲል የዶይቸ ቬለው መሐመድ ኦዶው ከሞቃዲሾ ዘግቧል።   

መሐመድ ኦዶው/ይልማ ኃይለ ሚካኤል 
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ነጋሽ መሐመድ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW