1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለንደን፤ ለሶማሊያ ቀዉስ ተጨማሪ 900 ሚሊየን ዶላር ያስፈልጋል

ሐሙስ፣ ግንቦት 3 2009

የብሪታንያ እና የምሥራቅ አፍሪቃ ሐገራት መሪዎች፤ የአዉሮጳ ሕብረት፤ የአፍሪቃ ሕብረት፤ የተባበሩት መንግሥታት እና የሌሎች ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተጠሪዎች የተካፈሉበት ጉባኤ የሶማሊያ ጦርነትና ረሐብ የሚወገድበትን ሥልት ይቀይሳል፤ ዕርዳታም ያሰባስባል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል።

Großbritannien Somalia-Konferenz
ምስል picture-alliance/AP Photo/J. Hill

MMT (Q&A) II. London Somalia konferenz - MP3-Stereo

This browser does not support the audio element.

የተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬሽ እና የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬሳ ሜይ በድርቅ ክፉኛ ለተጎዳችዉ ሶማሊያ ተጨማሪ የርዳታ ጥሪ አቀረቡ። ባለስልጣናቱ በሱማሊያ ጉዳይ ለንደን ላይ ለሚካሄደዉ ጉባኤ በሀገሪቱ 439 ሺህ የሚሆን ሕዝብ ለሚገድል ረሃብ፤ 6 ሚሊየን የሚሆነዉም ለከፋ የምግብ እጥረት መጋለጡን አመልክተዋል። ሶማሊያን ከምትገኝበት ቀዉስ ለማዉጣትም በዚህ ዓመት ተጨማሪ የ900 ሚሊየን ዶላር ርዳታ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል። ። እንዲያም ሆኖ በተደጋጋሚ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለችግሯ ስብሰባ የሚካሄድላት ሶማሊያ ለምትገኝበት የድርቅም ሆነ ፖለቲካዊ ቀዉስ ሁነኛ መፍትሄ ከአሁኑ ስብሰባ መገኘት መቻሉን የሀገሪቱን ሁኔታ በቅርበት የሚከታተሉት ቀድሞ በተመድ የሱዳን ልዩ ልዑክ የነበሩት ፒተር ሹማን ይጠራጠራሉ።

«በዓለም አቀፍ ደረጃ በጉባኤ የተገኙት አዳዲስ ተሳታፊዎች ለቀዉሱ እዉነተኛ ፖለቲካዊ አቀራረብ መጠቀም መቻላቸዉን እጠራጠራለሁ። ድርቁ አንድ ጉዳይ ነዉ። አሸባብ ደግሞ ሌላኛዉ ነዉ። በዚያም ላይ ያልተፈታ አጠቃላይ የመንግሥት ችግር ሶማሊያ ዉስጥ አለ። ስለዚህ ፖለቲካዊ ጉዳዩን አሳንሶ ሁሉንም ነገር ወደድርቁ የመወርወሩ ነገር ያሳስበኛል። በዚህም ምክንያት ይህ ጉባኤ ዉስብስቡን የሶማሊያን ቀዉስ ለመፍታት ወደሚያስችል መንገድ ያቀርበናል ብዬ አላስብም።»

ከፀጥታዉ ችግር በተጨማሪ በድርቅ በተጠቃችዉ ሶማሊያ በቅርቡ የተቀሰቀሰዉ የኮሌራ ወረርሽኝ እስካሁን የ690 ሰዎችን ሕይወት ቀጥፏል። በኮሌራ የተያዙት ሰዎችም ቁጥር እስከ መጪዉ ሰኔ መጨረሻ ቀናት ድረስ 50 ሺህ ሊደርስ እንደሚችል የዓለም የጤና ድርጅት ዛሬ ያወጣዉ መግለጫ ያመለክታል። 

ምስል Getty Images/AFP/P. Moore

 የተቀናቃኝ  ኃይላት  ዉጊያ፤ ሽብርና የዉጪ ጣልቃ ገብ ጦር ዘመቻ ያወደማትን ሶማሊያን እንደ ሐገር ለማቆም ይረዳል የተባለ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ዛሬ ለንደን-ብሪታንያ ዉስጥ ተጀምሯል። የብሪታንያ እና የምሥራቅ አፍሪቃ ሐገራት መሪዎች፤ የአዉሮጳ ሕብረት፤ የአፍሪቃ ሕብረት፤ የተባበሩት መንግሥታት እና የሌሎች ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተጠሪዎች የተካፈሉበት ጉባኤ የሶማሊያ ጦርነትና ረሐብ የሚወገድበትን ሥልት ይቀይሳል፤ ዕርዳታም ያሰባስባል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል። ብሪታንያ ሥለ ሶማሊያ ጉዳይ የሚነጋገር ዓለም አቀፍ ጉባኤ ስታስተናግድ በዓምስት ዓመት ዉስጥ ያሁኑ ሁለተኛዉ ነዉ። የጉባኤዉን ሒደት የተከታተለዉ የለንደኑ ወኪላችን ድልነሳ ጌታነሕ እንደሚለዉ ግን ጉባኤዉ ለሶማሊያ ዉስብስብ ችግር ሁነኛ መፍትሔ ማመላከቱ አጠራጣሪ ነዉ። 

ድልነሳ ጌታነሕ

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ 
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW