1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሶማሊያ ጠቅላይ ምኒስትር ሐሳን አሊ ኻይሬ ከሥልጣን ተነሱ

ቅዳሜ፣ ሐምሌ 18 2012

የሶማሊያ ምክር ቤት የአገሪቱን ጠቅላይ ምኒስትር ሐሳን አሊ ኻይሬ የመተማመኛ ድምፅ በመንፈግ ከሥልጣን አነሳ። በምክር ቤቱ ጠቅላይ ምኒስትሩን ከሥልጣን ለማንሳት የቀረበው የውሳኔ ሐሳብ በ170 ድጋፍ በ8 ተቃውሞ ጸድቋል።  

Außenminister Gabriel besucht Somalia
ምስል picture alliance/dpa/M.Gambarini

የሶማሊያ ምክር ቤት የአገሪቱን ጠቅላይ ምኒስትር ሐሳን አሊ ኻይሬ የመተማመኛ ድምፅ በመንፈግ ከሥልጣን አነሳ። በምክር ቤቱ ጠቅላይ ምኒስትሩን ከሥልጣን ለማንሳት የቀረበው የውሳኔ ሐሳብ በ170 ድጋፍ በ8 ተቃውሞ ጸድቋል።  

የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ መሐመድ ሙርሳል "ጠቅላይ ምኒስትሩ ለፌድራል እና የክልል መንግሥታት የጸጥታ ቁጥጥሩን የሚያጠብቅ ብሔራዊ የጸጥታ ኃይል ሳያዋቅሩ ቀርተዋል" ሲሉ ከሥልጣን የተነሱበትን ምክንያት አብራርተዋል።

የጠቅላይ ምኒስትሩን ከሥልጣን መነሳት ፕሬዝዳንት መሐመድ አብዱላሒ መሐመድ መቀበላቸውን አረጋግጠዋል። ፕሬዝዳንቱ በአፋጣኝ አዲስ ጠቅላይ ምኒስትር እንደሚሾሙ ከምክር ቤቱ ውሳኔ በኋላ ባወጡት መግለጫ አሳውቀዋል።

ጠቅላይ ምኒስትሩ ከሥልጣን መነሳታቸው ከተረጋገጠ በኋላ መጪው የሶማሊያ ምርጫ በሚካሔድበት የጊዜ ሰሌዳ ጉዳይ በምክር ቤቱ ውዝግብ ተነስቷል።

ሐሳን አሊ ኻይሬ፣ ፕሬዝዳንት መሐመድ አብዱላሒ መሐመድ እና የክልል መንግሥታት መሪዎች በመጪው ጥር 2013 ዓ.ም.  የተቀጠረው ምርጫ በታቀደለት ጊዜ ይካሔድ አይካሔድ በሚለው ጉዳይ ላይ ውይይት ሲያደርጉ ሰንብተዋል።

ሐሳን አሊ ኻይሬ የሶማሊያ ጠቅላይ ምኒስትር ሆነው ሥልጣን የጨበጡት የካቲት 2009 ዓ.ም. ነበር።

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW