1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሶማሌላንድ የምርጫ ዉጤት እና አንድምታዉ

ማክሰኞ፣ ኅዳር 10 2017

የሶማሌላንድ፤ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ አብዲራህማን መሀመድ አብዱላሂ ምርጫዉን አሸነፉ። ባለፈዉ ሳምንት ረቡዕ ፕሬዚዳንትታዊ ምርጫን ያካሄደችዉ በተካሄደዉ ምርጫ «ኢሮ» በሚል ቅፅል ስያሜያቸዉ የሚታወቁት ሶማሌላንድ ፕሬዚዳንት 63.92 በመቶ ድምፅን በማግኘት የሶማሌላንድ ስድስተኛ ፕሬዚዳንት መሆናቸዉን የሃገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን አስታዉቋል።

ሶማሌላንድ
ሶማሌላንድምስል Eshete Bekele/DW

የሶማሌላንድ የምርጫ ዉጤት እና አንድምታዉ

This browser does not support the audio element.

የሶማሌላንድ የምርጫ ዉጤት እና አንድምታዉ

በሶማሌላንድ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ፤ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ አብዲራህማን መሀመድ አብዱላሂ አሸነፉ። ባለፈዉ ሳምንት ረቡዕ ፕሬዚዳንትታዊ ምርጫን ያካሄደችዉ ሶማሌ ላንድ  «ኢሮ» በሚል ቅፅል ስያሜያቸዉ የሚታወቁት አዲሱ ፕሬዚዳንት 63.92  በመቶ ድምፅን በማግኘት የሶማሌላንድ ስድስተኛ ፕሬዚዳንት መሆናቸዉን የሃገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ዛሬ አስታዉቋል። ባንጻሩ ተሰናባቹ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቤሂ 34.81 በመቶ ድምፅ ማግኘታቸዉ ይፋ ሆንዋል።

የሶማሌላንድ የምርጫ ዉጤት ይፋ እንደሆነ በሶማሊያ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ለሶማሊላንድ እና ለተመራጩ ፕሬዚዳንት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት በኤክስ ገጹ አስፍሯል። «የሶማሌላንድ የምርጫ ግሩም ታሪክ፤ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር» ሲል የአሜሪካ ኤንባሲ ዉጤቱን እና ሂደቱን አርአያ የሚሆን ብሎታል።

የሶማሌላንድ የምርጫ ዉጤት አንደምታዉ እንዴት ይገመገማል፤ የሶማሌላንድ እና የኢትዮጵያ የመግባብያ ስምምነትአቅጣጫዉ ይቀየር ይሆን ? የቀጠናዉ ዉጥረት ይረግብስ ይሆን? የፖለቲካ ተንታኝን አነጋግረናል። 

አዜብ ታደሰ 
ታምራት ዲንሳ 
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW