ፕሬዝዳንት ቢሂ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር ይነጋገራሉ
ማክሰኞ፣ ጥር 8 2010ማስታወቂያ
ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ሶማሌላንድን የሚመሩት ሙሳ ቢሂ በፕሬዝዳንት ዘመናቸው ቁልፍ አጀንዳቸው የሆነው ራሷን እንደ ሀገር የምትቆጥረውን ሶማሌላንድ ዓለም አቀፍ እውቅና እንድታገኝ ማድረግ ነው፡፡ ለዚህ ጥረታቸው ትልቁ ተግዳሮት ሶማሌላንድን እንደ አንድ ግዛቷ የምትቆጥረው ሶማሊያ እንደሆነች ዘገባዎች ያመላክታሉ፡፡
ለሶማሌላንድ እስካሁን ድረስ ይፋዊ ዕውቅና የሰጠ ባይኖርም ኢትዮጵያን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መስርተው ቆይተዋል፡፡ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እንደውም በበርበራ ወደብ የጦር ሰፈር ለመገንባት ስምምነት ፈጽማለች፡፡
የፕሬዝዳንት ቢሂ የኢትዮጵያ ጉብኝት በአፍሪቃ ቀንድ የሰላም ሁኔታ እና ሌሎችም የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ያተኩራል ተብሏል፡፡ የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል፡፡
ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
ተስፋለም ወልደየስ
ነጋሽ መሐመድ