የሶማሌና የአማራ ክልልሎች ግንኙነት
ዓርብ፣ ሐምሌ 12 2011![Äthiopien Empfang von Mustafa Mohammed Omer](https://static.dw.com/image/49652900_800.webp)
ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሠ መስተዳድር ሙስጠፋ መሐመድ የመሩት የሶማሌ ክልል የባለስልጣናትና የሐገር ሽማግሌዎች ቡድን የአማራ ክልልን ለሶስት ቀን ለመጎብኘት ዛሬ ባሕርዳር ገብቷል።ከ100 በላይ ፖለቲከኞችን፣ የመስሪያ ቤት ኃላፊዎችንና የጎሳ መሪዎችን የያዘዉ የሶማሌ ክልል የመልዕክተኞች ጓድ በአማራ ክልል የሚገኙ ተቋማትን ይጎበኛል፤ ከሕዝብና ከባለስልጣናት ተወካዮች ጋር ይነጋገራል፣ በዩኒቨርስቲ ምርቃ ድግስ ላይ ይገኛልም።ጉብኝቱ የሁለቱን ክልሎች ሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር ይጠቅማል ተብሏል።
ዓለምነዉ መኮንን
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሰ