1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ራሱን (IS) የሚለው ቡድን በሱማሊያ እየተጠናከረ መሆኑ ተገለጸ

ገበያው ንጉሤ
ረቡዕ፣ መስከረም 8 2017

ራሱን እስላማዊ መንግሥት በማለት የሚጠራው ቡድን፤ በእንግሊዝኛ ምህጻሩ (IS) ቀድሞ ከነበረባቸው ስፍራዎች ተሸንፎ ቢባረርም በሶማሊያ ግን እየተጠናከረ መምጣቱ ተገልጧል ። የሱማሌና ሌሎች መንግስታት በጋራና በተቀናጀ ርምጃ እንቅስቃሴውን እንዲገድቡም ዓለማቀፉ ጥሪ ተላልፏል።

Somalias Bildungsministerium in Mogadischu von zwei Explosionen getroffen
ምስል ABDIHALIM BASHIR/REUTERS

የሶማሌው አይሲስ እንቅስቃሴ ላይ ርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ተላልፏል

This browser does not support the audio element.

ራሱን እስላማዊ መንግሥት በማለት የሚጠራው ቡድን፤  በእንግሊዝኛ ምህጻሩ (IS) ቀድሞ ከነበረባቸው ስፍራዎች ተሸንፎ ቢባረርም በሶማሊያ ግን እየተጠናከረ መምጣቱ ተገልጧል ። ግጭት ጦርነቶችን የሚተነትነው ዓለማቀፉ ድርጅት (International Crisis Group)ባለፈው ሳምንት መስከረም አንድ ቀን ባወጣው መግለጫ ይህንኑ አረጋግጧል።  እስላማዊ መንግስት በምስራቅ አፍሪቃ በተለይም በሱማሊያ የፑንትላንድ ራስ ገዝ አስተዳደር ተጠናካሮ እየወጣ መሆኑን ጠቅሷል ።  የሱማሌና ሌሎች መንግስታት በጋራና በተቀናጀ ርምጃ እንቅስቃሴውን እንዲገድቡም ዓለማቀፉ ድርጅት ጥሪ አስተላልፏል።

በግጭት ጦርነቶች ዙሪያ የሚሰራው አለማቀፍ ድርጅት International Crisis Group የሚባለው፤ ባለፈው ሳምንት መስከረም አንድ ቀን ባወጣው መግለጫ፤ እስላማዊ መንግስት በእንግሊዝኛ ምህጻሩ IS የሚባለው አሸባሪ ድርጅት በምስራቅ አፍሪካ በተለይም በሱማሊያ  የፑንትላንድ ራስ ገዝ አስተዳደር ተጠናካሮ እየወጣ መሆኑን በማሳየት፤  የሱማሌና ሌሎች መንግስታት በጋራና በተቀናጀ እርምጃ  እንቅስቃሴውን ይገድቡትና ያስቆሙት ዘንድ ጥሪ አቅርቧል።

እስላማዊ መንግስት ወይም አይ ኤስ ከዓመታት በፊት በተለይ በሶሪያና ኢራቅ ተስፋፍቶና ተጠናክሮ ለአለማዊው ወይም ሴኩላሩ የአለም ስራት ስጋት እስከመሆን ደርሶ የነበር መሆኑ አይዘነጋም። መንግስታት በግልና በጋራ ባክሄዱት የጸረሽብር ዘመቻ የቡድኑን እንቅስቃሴ በማስቆም በተጠቀሱት አገሮች ከነበረው ይዞታ እንዲነቀልና እንዲበታተን ቢደረግም፤ በሌሎች አገሮች በተለይም በአፍሪካ የተለያዩ አካባቢዎች ግን በዝቅተኛ ደረጃም ቢሆን እንደሚንቀሳቀስና እየተነሳቀስም እንደሆነ ነው የሚነገረው።

የሶማሌው አይሲስ ዓለማቀፍ የድርጅቱ አስተባባሪ እየሆነ ስለመምጣቱ

ቡድኑ በሶማሊያም ከዓመታት በፊት በአካባቢው በስፋት ከሚንቀሳቀሰው አልሸባብ በወጡ ሰዎች ከተመሰረተ በኋላ፤ በሱማሊያ መነግስትና ከራሱ አልሸባብ በሚሰነዝርበት ጥቃት ተዳክሞ የነበረ ቢሆንም፤ ባህኑ ወቅት ግን ምንም እንኳ እንዳልሸባብ ብዙ ጥቃቶችን እየፈጸመ ባይሆንም፤ ኅልውናውን አስጠብቆ፤ በተለይ በፑንትላንድ ግዛት ተጠናክሮ እንደሚገኝና በሌሎች የአፍርካ አገሮች የድርጅቱ ህዋሶችና ቅርንጫፎችም  እንደማዕከል ሆኖ እያገልገለ እንደሆነ ዘገባው  አመላክቷል።  በሪፖርቱ ላይ እንደሰፈረውና  የክራይሥ ግሩፕ የምስራቅ አፍርካ ተንታኙ ሚስተር ኦማር ማህሙድ ለዲደብለው እንደገለጹት፤ ባሁኑ ወቅት የሶማሌው አይሲሲ በራሱ ፋይናንስ እያመነጨና በአፍሪካም ይሁን በሌሎች አገሮች ለሚገኙ የድርጅቱ ህዋሶችና ቅርንጫፎች እየረዳ ነው። በተጨማሪም የሶማሌው አይሲስ መሪ አብዱልቃዲር ሙኒን የአለማቀፉ አይሲሲ መሪ ወይም ካሊፍ ተደርገው እንደሚታዩና ከጎረበትና ከሩቅ አገሮች ወደ ደርጅቱ የሚገቡ ተዋጊዎች ቁጥርም ቀስ  በቀስ እየጨመረ እንደሆነ ተገልጿል።

የአፍሪቃ ኅብረት የሶማሊያ ሰላም አስከባሪ ጓዶች ። ፎቶ፦ ከማኅደርምስል ZUMA Press/IMAGO

ድርጅቱ የደቀነው አሁናዊ ስጋት

ያም ሆኖ ግን ወታደራዊ ጥቃት በመፈጸምና ጉዳት በማድረስ በኩል ካአልሸባብ ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ በመሆኑ በዙም አስጊ እንዳልሆነ ነው የሚነገረው። ሚስተር ኦማር ግን የአስጊነት ደረጃ የሚለካው አሁን ጥቃት ለመፈጸም ባለው ብቃት ብቻ ሳይሆን ይልቁንም ሌሎቹ የስላሚክ ስቴቶች ህልውና እንዲቀጥል ለማድረግ በሚጫወተው ሚና ነው ባይ ናቸው።

የኢትዮጵያና ሶማሊያ አለመግባባትና ውጥረት በአይሲስ እንቅስቃሴ ላይ ያለው ተጽኖ

ሚሰር ኦማር በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ፤ ሶማሊያና ግብጽ መካከል የተፈጠረው አለመግባባትና በአካባቢው ያለው ውጥረት በአይሲስ እንቅስቃሴ ላይ ሊይሳድር የሚችለውን ተጽኖም ተጠይቀው ነበር፤  "በአገሮች መክከል ያለው የጂኦ ፖለቲካ ውጥረት በአይሲሲ ሚና ብዙም ተጽኖ የሚኖረው አይመስለኝም፤ ከዚያ ይልቅ በየአገሮቹ ባሉ የፖለቲካ ውጥረቶችና ግጭቶች ነው ተጠቃሚ የሚያሆነው” በማለት የጂኦፖለቲካው ውጥረት ከአይሲስ  ይልቅ አልሸባብን ሊጠቅም እንደሚችል ገልጸዋል። 

ኢትዮጵያ እና ራሷን ሶማሌላንድ ሪፐብሊክ ብላ የምትጠራው ግዛት ስምምነት ካደረጉ በኋላ ውጥረቱ እንዳየለ ነውምስል TIKSA NEGERI/REUTERS

የድርጅቱን መስፋፋት ለመግታት ምን መደረግ አለበት?

ሚስተር ኦማር በሪፖርቱ የተጠቀሱትንና የዚህን ድርጅት እንቅስቃሴ ለመግታት ሊደረጉ ይገባቸዋል የተባሉትን ሶስት አበይት ምክረ ሀሳብቾንም ከዲደብሊው ጋር በነበራቸው ቆይታ ጠቅሰዋል፤ የመጀመሪያው አሉ ሚስተር ኦማር፤ " የመጀመሪያው የሶማሊያ አይሲስ የገቢ ምንጮችን ማድረቅ ነው። ይህ ግን በፑንት ላንድ አስተዳደር ብቻ ሚደረግ ባለመሆኑ  የሶማሊያ መንግስትና ሌሎችም ሊተባበሩና አብረው ሊሰሩ ይገባል። ሁለተኛው፤ ድርጅቱን የሚለቁ ግለስቦችን በቀናነት መቀበልና ማቋቋም ነው። ሶስተኛው፤ ድርጅቱንና የድርጅቱን አባላት አቅፎ ደግፎ የያዘውን ማህብረሰብ ቅሬታዎቹን በመስማት፤ ጥያቄዎቹን በመቀበልና ልማት በማስፋፍት  ከጉያው እንዲያወጣቸው ማድረግ ነው” በማለት ለሁሉም ግን  የአካባቢው መንግስታት ከራሳቸውም ከጎረበቶቻቸው ጋር በመታረቅ በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆን ያለባቸው መሆኑን ሚስተር ኦማር አጽንኦት ስተው ተናግረዋል።

ገበያው ንጉሤ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ፀሐይ ጫኔ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW