1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሶማሌ መስተዳድር ፖለቲካዊ ቀዉስ

ሐሙስ፣ ጥር 16 2011

የርዕሠ-መስተዳድር ሙስጠፋ መሐመድ የሕግና የሠብአዊ መብት ጉዳዮች አማካሪ አቶ ጀማል ድሬይ እንደሚሉት አራተኛ ወሩን የያዘዉን መስተዳድር ለማፍረስ የቀድሞ ባለሥልጣናት፣ የክልሉ ገዢ ፓርቲ የኢሶሕዴፓ ሊቀመንበር ና የኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች ባለሥልጣናት ባንድ አብረዉ እየዶሎቱ ነዉ።

Jemal Deere Kelif
ምስል privat

(Q&A) Somale region political crisuis-Jemal Dire - MP3-Stereo

This browser does not support the audio element.

የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ርዕሠ መተዳድር የአብዲ መሐመድ ዑመር ደጋፊዎች አዲሱን የክልሉን ርዕሠ መስተዳድር ሙስጠፋ መሐመድ ዑመርን ከስልጣን ለማዉረድ እያሴሩ መሆናቸዉን አንድ የክልሉ ባለስልጣን አጋለጡ።የርዕሠ-መስተዳድር ሙስጠፋ መሐመድ የሕግና የሠብአዊ መብት ጉዳዮች አማካሪ አቶ ጀማል ድሬይ እንደሚሉት አራተኛ ወሩን የያዘዉን መስተዳድር ለማፍረስ የቀድሞ ባለሥልጣናት፣ የክልሉ ገዢ ፓርቲ የኢሶሕዴፓ ሊቀመንበር ና የኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች ባለሥልጣናት ባንድ አብረዉ እየዶሎቱ ነዉ።የሕግና የሰብአዊ መብት አማካሪዉ አክለዉ እንዳሉት  ከሴረኞቹ መካከል አንዳዶቹ በፌደራሉ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ክስ የተመሠረተባቸዉ ናቸዉ።አማካሪ ጀማል ድሬይን በስልክ አነጋግሬያቸዋለሁ።

ነጋሽ መሐመድ

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW