1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የሶማሌ ክልል ዋና ከተማ ጅግጅጋ ነዋሪዎች ስለ ምርጫ ምን ይላሉ?

መሳይ ተክሉ
እሑድ፣ ግንቦት 23 2018

የሶማሌ ክልል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ላሉት 23 መቀመጫዎች ገዢው ብልፅግና ፓርቲን ጨምሮ የ12 የፖለቲካ ፓርቲዎች ዕጩዎች እና አራት የግል ተወዳዳሪዎች ለምርጫ ቀርበዋል። ለክልሉ ምክር ቤት 273 መቀመጫዎች የሚወዳደሩት 12 የፖለቲካ ፓርቲዎች ዕጩዎች እና 39 የግል ተወዳዳሪዎች ናቸው።

ጅግጅጋ ከተማ
የሶማሌ ክልል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ላሉት 23 መቀመጫዎች ገዢው ብፅግና ፓርቲን ጨምሮ የ12 የፖለቲካ ፓርቲዎች ዕጩዎች እና አራት የግል ተወዳዳሪዎች ለምርጫ ቀርበዋል። ምስል፦ Mesay Teklu/DW

የሶማሌ ክልል ዋና ከተማ ጅግጅጋ ነዋሪዎች ስለ ምርጫ ምን ይላሉ?

This browser does not support the audio element.

ነገ ለሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ለዶይቼ ቬለ አስተያየት የሰጡ የጅግጅጋ ነዋሪዎች ገልፀዋል። በሀገሪቱ በ1997 የተካሄደውን ሀገራዊ ምርጫ በበጎ የሚያስታውሱት የጅግጅጋ ነዋሪው አቶ ጉተማ ዘውዴ በበኩላቸው አስቻይ ሁኔታ ኖሮ ሳይሆን ወቅቱን መጠበቅ ግድ ስለሆነ የተካሄደ ነው ብለዋል።

ለመራጭነት የሚያበቃውን ካርድ የወሰደ ማንኛውም ሰው የሚጠቅመውን አስቦ መምረጥ እንዳለበት የሚናገረው የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲው መምህር ሱራፌል መኩርያ መምረጥ ስልጣን ከሚረከበው አካል ጋር አብሮ መስራት ማለት እንደሆን ገልፃል። አስተያየት ሰጭዎቹ መምረጥ ካለመምረጥ የተሻለ መሆኑን ሀሳባቸውን አጋርተዋል።

የሶማሌ ክልል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ላሉት 23 መቀመጫዎች ገዢው ብልፅግና ፓርቲን ጨምሮ የ12 የፖለቲካ ፓርቲዎች ዕጩዎች እና አራት የግል ተወዳዳሪዎች ለምርጫ ቀርበዋል።

ለክልሉ ምክር ቤት መቀመጫዎች የሚወዳደሩት 12 የፖለቲካ ፓርቲዎች ዕጩዎች እና 39 የግል ተወዳዳሪዎች ናቸው። የሶማሌ ክልል ምክር ቤት 273 መቀመጫዎች አሉት።

ለሰባተኛው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ለክልል ምክር ቤት መቀመጫዎች ከሚወዳደሩት መካከል ነፃነትና እኩልነት ፓርቲ፣ የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር፣ የምዕራብ ሶማሌ ዲሞክራቲክ ፓርቲ እና ኅብረት ለዲሞክራሲና ለነፃነት ፓርቲ ይገኙበታል። በግል የሚወዳደሩ 39 ዕጩዎችም ቀርበዋል። የሶማሌ ክልል ብዛት ያላቸው የግል ተወዳዳሪዎች በማስመዝገብ ከተቀሩት ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች ከፍተኛ ብልጫ አለው። 

መሳይ ተክሉ
እሸቴ በቀለ 
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW