ፕሬዝደንቷ የለቀቁት የሶማሌ ክልል
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 1 2010ማስታወቂያ
ይህን የገለፁት ክልሉን ወክለው የፌደራል ምክር ቤት አባል የነበሩት እና አሁን በስደት የሚገኙት አቶ ጀማል ዲሪዬ ኸሪፍ ናቸው። ለሁለት የአገልግሎት ዘመን ተመርጠው በጥቅሉ ስድስት ዓመት ከመንፈቅ በምክር ቤት የሶማሌ ክልል የሕዝብ ተወካይ የነበሩት አቶ ጀማል፤ በክልሉ ነገሮች የሚያመሩበትን አቅጣጫ በመረዳታቸው ለመሰደድ መገደዳቸውን ለዶይቼ ቬለ ገልጸዋል። አብዲ ኢሌ በመባል የሚታወቁት የሶማሌ ክልል ፕሬዝደንት ትናንት ከስልጣናቸው መልቀቃቸው ተነግሯል። ፕሬዝደንቱ አቤቱታ ሲቀርብባቸው መቆየቱን በማንሳት ከአቶ ጀማል ጋር አችር ቃለ ምልልስ አድርገናል። ፕሬዝደንቱን ለዚህ ያበቃቸው ግፊት ኖሮ ይሆን በሚል ላስቀደምኩት ጥያቄ ምላሽ በመስጠት ይጀምራሉ።
ሸዋዬ ለገሠ
አርያም ተክሌ