1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሶማሌ ዑጋዛዊ ምክር ቤት የምርጫ ቦርድን ውሳኔ ተቃወመ 

ማክሰኞ፣ መጋቢት 21 2013

ምርጫ ቦርድ የአፋርና የሶማሌ ክልሎች በሚወዛገቡባቸው ቀበሌዎች "ሊከፈቱ የነበሩ 30 የምርጫ ጣቢያዎች በአካባቢው እንዳይቋቋሙ" መወሰኑ እያወዛገበ ነው። "የምርጫ ጣቢያዎች የአስተዳደር ወሰኖችን የሚወስኑ መገለጫዎች ባይሆኑም ቦርዱ ምርጫ በምንም መልኩ የሰላም መደፍረስ ምክንያት እንዳይሆን" ያስተላለፈውን ውሳኔ የሶማሌ ዑጋዛዊ ምክር ቤት ተቃውሟል

Äthiopien I Mohamed Muse
ምስል Mesay Teklu/DW

የሶማሌ ዑጋዛዊ ምክር ቤት የምርጫ ቦርድን ውሳኔ ተቃወመ 

This browser does not support the audio element.

የሶማሌ ዑጋዛዊ ምክር ቤት ምርጫ ቦርድ በሶማሌ እና አፋር ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች በሚገኙ ስምንት ቀበሌዎች ያሳለፈውን ውሳኔ በሚመለከት የክልሉ መስተዳድር ላቀረበው ጥያቄ ቦርዱ የሰጠውን ምላሽ ተቃወመ፡፡ ውሳኔውን “ግጭት ቀስቃሽ” ሲል አውግዞታል ፡፡ 

የሶማሌ ዑጋዛዊ ምክር ቤት ተጠሪ አቶ መሀመድ ሙሴ ጌሪ ለዶይቼ ቬለ በሰጡት መግለጫ በቅርቡ ምርጫ ቦርድ ያሳለፈውን ውሳኔ እንደሚቃወሙ ፣ በጉዳዩ ላይ የክልሉ መንግስት ለቦርዱ ያቀረበውን ጥያቄ እንደሚደገፉ ገልጠው “ግጭት ቀስቃሽ” ያሉትን የቦርዱ ውሳኔ ቦርዱ እንዲመረምር ጠይቀዋል፡፡

ምስል Mesay Teklu/DW

ቦርዱ በስምንቱ የምርጫ ጣቢያዎች የሚገኙ ነዋሪዎች በአቅራቢቸው ባለ ምርጫ ጣቢያ እንዲመርጡ ይደረጋል የሚለውም ትክክል አለመሆኑን አቶ መሀመድ ተናግረዋል፡፡
የሲቲ ዞን ነዋሪው አቶ አደም ፈንታሌ በበኩላቸው “በብዙ ችግር ውስጥ ባለችው ሀገር ላይ ሌላ ችግር መሆን አንፈልግም በሰላማዊ መንገድ ላቀረብነው ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ ይሰጠን” ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

የኢትዮጵ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ  በሶማሌ እና አፋር ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች በሚገኙ ስምንት ቀበሌዎች ምርጫ ዙርያ ያሳለፈውን ውሳኔ በሚመለከት ከሶማሌ ክልላዊ መስተዳድር ለቀረበለት ጥያቄ ምላሽ መስጠቱ የሚታወስ ነው፡፡

መሳይ ተክሉ
ሸዋዬ ለገሠ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW