1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሶማልያው ፕሬዝዳንት መሐመድ አብዱላሒ መሐመድ ኤርትራ ገቡ

እሑድ፣ መስከረም 24 2013

የሶማልያው ፕሬዝዳንት መሐመድ አብዱላሒ መሐመድ ዛሬ ማለዳ አስመራ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ተቀብለዋቸዋል።ፎርማጆ ወደ አስመራ ያቀኑት ለሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት መሆኑን ቪላ ሶማሊያ ተብሎ የሚጠራው የፕሬዝዳንቱ ጽህፈት ቤት አስታውቋል። 

Bildkombo l Somalischer Präsident Mohamed Abdullahi Mohamed und Eritreische Präsident Isaias Afwerki

የሶማልያው ፕሬዝዳንት መሐመድ አብዱላሒ መሐመድ ዛሬ ማለዳ ኤርትራ ገቡ። ፎርማጆ በሚል የቅጽል ስማቸው የሚታወቁት ፕሬዝዳንት መሐመድ አብዱላሒ መሐመድ አስመራ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ተቀብለዋቸዋል።

ፎርማጆ ወደ አስመራ ያቀኑት ለሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት መሆኑን ቪላ ሶማሊያ ተብሎ የሚጠራው የፕሬዝዳንቱ ጽህፈት ቤት አስታውቋል። በሶማሊያ እና በኤርትራ የሁለትዮሽ ግንኙነት እና በቀጠናው ጉዳዮች ላይ ፕሬዝዳንት ፎርማጆ እና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እንደሚመክሩ የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ይፋ ያደረገው አጭር ማብራሪያ ይጠቁማል። 

በኤርትራ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ሥራዎችንም የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ይጎበኛሉ ተብሏል። ፎርማጆች ባለፉት ሁለት አመታት ወደ አስመራ ሲያመሩ ይኸ የመጀመሪያቸው አይደለም። 
ባለፈው ጥር ወር እንኳ ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ፕሬዝዳንት መሐመድ አብዱላሒ መሐመድ እና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በዚያው በአስመራ ተገናኝተው ነበር። 

ኤርትራ እና ሶማሊያ ለረዥም አመታት ተቋርጦ የቆየ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ማረቅ የጀመሩት ባለፈው ሐምሌ 2010 ዓ.ም ፎርማጆ ወደ አስመራ ተጉዘው ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ ከተገናኙ በኋላ ነው። 
ፕሬዝዳንት መሐመድ አብዱላሒ መሐመድ ወደ አስመራ ከማቅናታቸው በፊት በደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ የሱዳን መንግሥት ከአማጺያን የሰላም ስምምነት ትናንት ቅዳሜ ሲፈራረም ተገኝተዋል። 

እሸቴ በቀለ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW