1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሶማልያ ምርጫና የዓለምአቀፉ ማህበረሰብ አስተያየት

ሰኞ፣ ግንቦት 8 2014

ከ2012 እስከ 2017 ዓም ድረስ ሶማሊያን በፕሬዘንትነት የመሩት ሀሳን ሼህ ሞሀሙድ ለመጭዎቹ አራት አመታት የአገሪቱ ፕሬዝድንት እንዲሆኑ የሶማሊያ ምክር ቤት ትናንት መርጧቸዋል። ሺክ ሞህሙድ የተመረጡት ከ36 ተወዳዳሪዎች መካከል በሶስተኛው ዙር ከፕሬዝዳንት አብዱላሂ ሞሃመድ ፎርማጆ ጋር ተወድድረው በሰፊ ልዩነት ነው።

Somalia Hassan Sheikh Mohamud
ምስል Abukar Mohamed Muhudin/AA/picture alliance

This browser does not support the audio element.

በሶማሊያ የፓርላማ አባላትም ሆኑ ፕረዝዳንቶች የሚመረጡት በቀጥታ በህዝብ መሆኑ ከቀረ አምሳ አመት አልፎታል። በ1990 የመጀመሪያዎቹ አመታት የፕሬዝዳንት ዚይድ ባሬ መንግስት ከተወገደ በኋላ፤ ጠንካራ ማእከላዊ መንግስት ኖሯት የማታውቀው ሶማሊያ፤ እስካሁንም ድረስ ህዝብ በቀጥታ የሚሳተፍበት የምርጫ ስራት ማደራጀት አልቻለችም። በምትኩ የጎሳ መሪዎች የፓርላማ አባላትን፤ የፓርላማ አባላት ደግሞ ፕሬዝድንቱን የሚመርጡበት ስራት ነው እየተሰራበት ያለው። ይህ አይነቱ አሰራር ዘንድሮ በቀጥታ የምርጫ ስራት ይተካል ተብሎ የነበር ቢሆንም፤ የአገሪቱ የጸጥታ ሁኒታና  በጎስዎች መክከል ያለው ፉክክርና ግጨት ይህን ማድረግ እንዳላስችለ ነው የሚታውቀው።  

የዘንድሮው ምርጫ ከአንድ አመት በፊት መድረግ ሲገባው እስካሁን በመዘግየቱ በተለይ በፕሬዝድንት አብዷልሂ ፎርማጆ ላይ ትችት አስከትሎ ነበር። ምርጫው እንዲደረግም  እንደ አሜሪካና የአውሮፓ ህብረት የመሳሰሉ አጋር መንግስታት ማሳስቢያ ሲያስተላልፉ የነበር ሲሆን፤ የዓለም የገንዘብ ድርጅት አዬኤምኤፍ  ምርጫው ካልተደረገ ለበጀት ድጎማ የሚሰጠውን 400 ሚሊዮን ዶላር  ሊያቋርጥ እንደሚችልም ገልጾ ነበር። 

የትናንቱን ምርጫና ውጤቱን ግን አጋር መንግስታትና የገንዘብ ተቋማቱ በአዎንታ የተቀበሉት መሆኑን እየገለጹ ነው። መንግስታቱ፤ ምርጫው በሰላም በመጠናነቀቁ ደስታቸውን በመግለጽ ለአዲሱ ተመራጭ ፕሬዝዳንት የእነኳን ደሳለዎ መልእክት እያስተላለፉ ሲሆን፤ የአውሮፓ ህብርት፤ ብርታኒያና የምስራቅ አፍርካ በየነ መንግስታት ኢጋድ የደስታ መልክት ካስተላለፉት ቀዳምዊዎቹ ናቸው። 

ሰላም የራቃት ሶማሊያ ግን በዚህ ምርጫና ውጤቱ የተረጋጋች መሆን መቻሏን ብዙዎች ይጠራጠራሉ። የምርጫው ሂደት እራሱ ከለመዱትና ከሚታወቁት ፖለቲካኞች ውጭ አዳዲስ ሰዎችን የማያመጣ በመሆኑ፤ ከአዲሱ ፓርላማና ፕሬዝዳንት አዲስ ነገር መጠበቅ ያስቸግራል ነው  የፖለቲካ  ተንታኞች የሚሉት። የቢቢስ ጋዜጠኛዋ  ወይዘሪት ቤላ ሃሣንም ምርጫው በትውውቅ እንጂ በሀሳብ ውድድርና በተቀመጠ መስፈርት የሚፈጸም ባለመሆኑ ብዙ ችግር አለበት፤ ለወጣቶችና ለሴቶችም ዕድል አይሰጥም ነው የምትለው፤ ‘ መራጮቹ ከመነሻው የባህል መሪዎች ናቸው። ለፓርላማ ተወካይ ሲመርጡ በትውውቅ ይወክለናል የሚሉትን እንጂ በመስፈርት አይደለም። ወጣቶችና ሴቶች በፓርላማ ለመመረጥ ያላቸው እድል ዝቅትኛ ነው፤  ምክኒይቱም ዓዛውንቶቹ እነሱን አይመርጧቸውም በማለት በዚህ ሁኒታ ተመርጠው የሚመጡት  ባለስልጣኖች የአገሪቱን ችግር ለመፍታት መቻላቸውን ትጠራጠረች`። 

የ 66 አመት አዛውንቱ ተመራጭ ሀሳን  ሼህ ሞሃሙድ ግን፤ አገራቸውን ከገባችበት ጥልቅ የደህንነትና የኢኮኖሚ ቀውስ ለማላቀቅ ጥረት እንደሚያደርጉ ነው በድል ብስራት ንግግርቸው የገለጹት። ሼህ ሞሃሙድ እ እ አ በ1912  ዓም ወደ ስልጣን ሲመጡም አልሸባብን በማስወገድ አገሪቱን የተረጋጋች ለማድረግና ኢኮኖሚያዋንም በማሳደግ ሶማሌያን  ከአመጽ አዙሪትና ድህነት ለማላቀቅ ቃል ገብተው የነበር ቢሆንም፤ ብዙም ግን ሳይሳካላቸው ክስልጣን እንደውረዱና በፕሬዝዳንት ፎርማጆ እንደተተኩ ነው የሚታወቀው። በአሁኑ ወቅት በአገሪቱም የተከሰተው ድርቅ ሚሊዮኖችን ለከፍተኝ እርሀብና ቸነፈር ዳርጓል፤ የኑሮው ውድነቱም ሰማይ ድርሷል ነው የሚባለው። ከሁሉም በላይ ግን አልቸባብ አሁንም ትልቁ የሶማሊያ ችግር መሆኑ ነው ዋናው ፈተና። እ እ እ በ2011 አም ከሞቃዲሾ ተገፍቶ ወቶ የንበረው አልሸባብ በአሁኑ ወቅት ከክተሞች ውጭ ባለው የሶማሊያ ግዛት ተንሰራፍቶ እንደሚገኝ እየተንገረ ሲሆን፤ ይህ ደግሞ ከሶማሊያ ዓልፎ ላካባቢው አገሮችም ስጋት መሆኑ ግልጽ ነው።።  ሚስተር አብዲ ስማተር የተባሉ የፖለቲካ ተንታኝም የአልሸባብን አደገኛነትና ለአዲሱ ፕረዝድንትም ዋናው ተግዳሮችሮት ህኖ የሚቀጥል መሆኑን ሲናገሩ፤ ‘አልሸባብ ችግርና ቀውስ ሲኖር ደስታው ነው ይጠቀምባቸዋል።  በኢትዮጵያም ሶማሊዎች ያሉ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፤ አለመረጋጋቱና ችግሩ  ደንበር ተሻጋሪም ሊሆን ይችላል።  ይህም በ ሁሉም ቦታ ሰላም ከሌለ ከአንዱ ቦታ ሰላም ሊኖር እንደማይችል ማሳያ ነው በማለት ፤ በአውሮፓ ህብረት የሚደገፈውና በአፍርካ ህብረት የሚመራውና 25 ሺ ይደርሳል የሚባለው የሰላም አሰክባሪ ሀይል እሳክሁን አልሸባብን ማሰወገድ ያልቻለበተን  ሁኒታ ይጠይቃሉ። 

ፕሬዝዳንት አብዱላሂ ፍሮማጆ በስልጣን ቆይታቸው ከጎረቤቶቻቸው፤ በተለይም ኬኤርትራና ኤትዮጵያ ጋር ጥሩ ግንኙነት የነበራቸው ሲሆን፤ አዲሱ ተመራጭ ፕሬዝዳንት ሼክ ሞሃሙድ ይህንን መልካም ጉርብትና ያስቀጥሉት አያስቀጥሉት ግን  ወደፊት የሚታይ ነው የሚሆነው። 

ገበያው ንጉሴ 

ልደት አበበ
ኂሩት መለሠ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW