የሶማልያ አዲሱ ፕሪዚደንት
ሐሙስ፣ መስከረም 3 2005ማስታወቂያ
ከቀናቶች በፊት የተደረገዉ የሶማልያ ፕሪዚዳንታዊ ምርጫ ከሶማልያ ዉጭ እንብዛም የማይታወቁትን የዩንቨርስቲ አስተማሪ ሐሰን ሼክ መሃመድን ይዞ ብቅ ብሎአል። አዲሱ የሶማልያ ፕሪዚደንት ሐሰን ሼክ መሃመድ በትምህርት ጉዳይ ላይ የማይናቅ ሚናን መጫወታቸዉ ይነገራል። የሶማልያዉ ፕሪዚዳንታዊ የምርጫ ዉጤት ምናልባትም በሙስና እና በንግዱ ዘርፍ በጎሰኝነት ጥቅምን በማካሄድ የሚታሙት እጩ ፕሪዚደንት እና የሽግግር ፕሪዚደንት የነበሩትን ሻሪፍ ሼክ አህመድን ስህተት ለማሳየት የታለመ ይሆናል። ሉድገር ሻዶምስኪ የሶማልያ አዲሱ ፕሪዚደንት በሚል የጻፈዉን ዘገባ ገመቹ በቀለ እንዲህ ያቀርበዋል
ገመቹ በቀለ
ሂሩት መለሰ