1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሶማልያ አገናኝ ቡድን በጣልያን

ዓርብ፣ ሰኔ 5 2001

በጣልያን ሮማ ዉስጥ ሶማልያ ላይ ያተኮረ የአገናኝ ቡድን የሁለት ቀናት ስብሰባ ተካሂዷል። ስብሰባዉን በሊቀመንበርነት የመሩት በሶማልያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ወኪል አምባሰደር አህመድ ኦልድ አብደላ ናቸዉ።

የሶማልያ የባህር ግዛትምስል AP

ከፍጻሜ በኋላ እንደተገለጠዉ በፕሪዝዳንት ሼኽ ሸሪፍ ሼህ አህመድ የሚመራዉ የሶማልያ የሽግግር መንግስት፤ በሃገር አቀፍ ማህበረሰብ በተባበሩት መንግስታት ድርጅ፤ በአፍሪቃ ህብረት በአረብ ሊግ እና በሙስሊም አገራት ጉባኤ እዉቅና ያገኘ መሆኑን ገልጠዉ ተጨባጭ እገዛ እንደሚያሻዉም አስገንዝበዋል። በሌላ በኩል ጣልያንን በመጎብኘት ላይ ያሉት የወቅቱ የአፍሪቃ ህብረት ሊቀመንበር የሊቢያዉ መሪ መሃመድ ጋዳፊ በሶማልያ የባህር ወንበዴዎችን ለመከላከል የተደረገዉን ዉይይት አስመልክቶ የባህር ዉንብድና ከሽብርተኝነት ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌለዉ እና ሶማሌዎች የባህር በራቸዉን ማስጠበቅ መብታቸዉ መሆኑን መግለጻቸዉ ተጠቅሶአል። ዝርዝሩን ተክለዝጊ ገብረየሱስ ከሮማ አጠናቅሮልናል

ተክለዝጊ ገብረየሱስ/ አዜብ ታደሰ/ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW