የሶርያ መንግሥት ከባለሥልጣናቱ የገጠመው ችግር
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 1 2004ማስታወቂያ
የውጭ የፖለቲካ ታዛቢዎች እንደሚሉት፡ የሶርያ ጠቅላይ ሚንስትር እና በሶርያ የተቃዋሚው ወገን ቃል አቀባይ ዘገባ መሠረት፡ ሁለት የመንግሥት ሚንስትሮች እና ሦስት ከፍተኛ የጦር ኃይሉ መኮንኖችም የከዱበት ድርጊት የፕሬዚደንት አሳድ መንግሥት ከውስጥ በገጠመው ተቃውሞ እየፈራረሰ መሆኑን ጠቋሚ ነው። ይህ በዚህ እንዳለ፣ የሶርያ ፕሬዝደንት በሽር አልአሰድ ላለፉት 17 ወራት የተነሳባቸዉ ህዝባዊ ተቃዉሞ ለመጨፍለቅ ቆርጠዉ መነሳታቸዉን አመለከቱ። ከሁለት ሳምንታት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ ያሉት አልአሰድ፤ የሶርያ ህዝብና መንግስት የአሸባሪዎችን ሀገርና ሽብርተኝነትን ለመዋጋት መዘጋጀታቸዉን መግለፃቸዉን ሮይተርስ የሀገሪቱን የዜና ወኪል በመጥቀስ ዘግቧል። አልአሰድ ስለጤና ማጣታቸዉም ሆነ ስለመገደላቸዉ ሲናፈስ የነበረዉን ወሬ ለጉብኝት ደማስቆ ከሚገኙት የኢራን የከፍተኛ ብሄራዊ የደህነት ምክር ቤት ኃላፊ ሳኢድ ጃሊሊ ጋ በመሆን በቴሌቪዥን ብቅ በማለትም መሠረተ ቢስ እንደሆነ አሳይተዋል።
ነቢዩ ሲራክ
አርያም ተክሌ
ሂሩት መለሰ