1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሻንጋይ ትብብር ጉባዔ

ሐሙስ፣ መስከረም 5 2015

ሩሲያ ዩክሬንን ከወረረች በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የሩሲያና የቻይና ፕሬዚደንቶች፣ ዛሬ ኡዝቤኪስታን ላይ ተገናኙ። ሁለቱ መሪዎች ወደ ቀድሞዋ የሶቭየት ህብረት ግዛት ኡዝቤኪስታን ያቀኑት በደህንነት ላይ በሚመክረዉ እና የሕንድ እና የመካከለኛው እስያ ሃገራት መሪዎች በሚገኙበት «የሻንጋይ ትብብር ድርጅት ጉባዔን» ለመካፈል ነዉ።

Usbekistan Samarkand | SGO Treffen | Xi Jinping, Wladimir Putin und Ukhnaagiin Khürelsükh
ምስል Alexandr Demyanchuk/Sputnik/REUTERS

ሩሲያ ዩክሬንን ከወረረች በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የሩሲያና የቻይና ፕሬዚደንቶች፣ ዛሬ ኡዝቤኪስታን ላይ ተገናኙ። ሁለቱ መሪዎች ወደ ቀድሞዋ የሶቭየት ህብረት ግዛት ኡዝቤኪስታን ያቀኑት በደህንነት ላይ በሚመክረዉ እና የሕንድ እና የመካከለኛው እስያ ሃገራት መሪዎች በሚገኙበት «የሻንጋይ ትብብር ድርጅት ጉባዔን» ለመካፈል ነዉ። በዩክሬን ጦርነት፣ ቻይና ለፑቲን ወገንተኝነትዋን እያሳየች እና ዩናይትድ ስቴትስና ኔቶ ዋነኛ ተጠያቂዎች እንደሆኑ እየገለፀች ነው። የሻንጋይ ትብብር ድርጅት ጉባዔ ነገ እንደሚጀምር የተዘገበ ሲሆን፤ በጉባዔዉ ላይ የቱርክ ፕሬዚዳንት ሬቺፕ ታይፕ ኤርዶጋን፣ የኢራኑ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይሲ እና የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ይገኛሉ። መሪዎቹ ከጉባዔዉ ትይይዩ የሁለት ዮሽ ስብሰባዎችን እንደሚያካሂዱም ተገልጿል።


አዜብ ታደሰ 

ኂሩት መለሰ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW