ሽብርተኝነት
በመኪና የሽብር ጥቃት በለንደን
ሰኞ፣ ሰኔ 12 2009ማስታወቂያ
በሰሜናዊ ለንደን በሚገኝ መስጊድ ጾማቸዉን ፈትተዉ ጸሎታቸዉን አድርሰዉ የሚመለሱ የከተማዋ ሙስሊም ነዋሪዎች ፖሊስ ሆን ተብሎ እንደተፈፀመ በጠረጠረዉ የመኪና ግጭት ጉዳት ደርሶባቸዋል። አንድ ሰዉ ሕይወቱ አልፏል። ጉዳት ከደረባቸዉ 10 ሰዎች የሁለቱ ከበድ እንደሚል ተነግሯል። እሳት ባስከተለዉ አደጋ ከሃዘን ያልተላቀቀችዉ የብሪታንያ ዋና ከተማ ለንደን ትናንት ማምሻዉን ደግሞ በመኪና ጥቃት ተደናግጣለች። ሃና ደምሴ ከለንደን ተከታዩን ዘገባ ልካለች።
ሃና ደምሴ
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ