1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሽታይንማየር የአፍሪቃ ህብረት ጉብኝት 

ረቡዕ፣ ጥር 22 2011

የህብረቱ ቃል አቀባይ ለDW እንደተናገሩት ሽታይንማየር የጀርመንን እና የአፍሪቃ ህብረትን ትብብር የማሳደግ ፍላጎት አላቸው። የጀርመን መንግሥት በአፍሪቃ ህብረት አማካይነት የአባል ሀገራት ልማትን ሊያፋጥኑ  በሚችሉ ጉዳዮች ላይ እየሰራ መሆኑንም ቃል አቀባይዋ ተናግረዋል።

Besuch von Bundespräsident Steinmeier in Äthiopien
ምስል Deutsche Botschaft in Addis Abeba

የሽታይንማየር የአፍሪቃ ህብረት ጉብኝት 

This browser does not support the audio element.

የጀርመን ፕሬዝዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር  በኢትዮጵያ ያደረጉትን የ3 ቀናት ጉብኝታቸውን ዛሬ አጠናቀው ወደ ጀርመን እየተመለሱ ነው። ፕሬዝዳንቱ ዛሬ እኩለ ቀን ላይ ከአዲስ አበባ ለመነሳት ቢያቅዱም አውሮፕላናቸው ባጋጠው የቴክኒክ ችግር ምክንያት ጉዞአቸው እንዲዘገይ መደረጉ ተዘግቧል።ሽታይንማየር ዛሬ ጠዋት በአፍሪቃ ህብረት ኮሚሽን በመገኘት ከህብረቱ ባለሥልጣናት እና ሠራተኞች ጋር የሀሳብ ልውውጥ አድርገዋል። የህብረቱ ቃል አቀባይ ለDW እንደተናገሩት ሽታይንማየር የጀርመንን እና የአፍሪቃ ህብረትን ትብብር የማሳደግ ፍላጎት አላቸው። የጀርመን መንግሥት በአፍሪቃ ህብረት አማካይነት የአባል ሀገራት ልማትን ሊያፋጥኑ  በሚችሉ ጉዳዮች ላይ እየሰራ መሆኑንም ቃል አቀባይዋ ተናግረዋል። ያነጋገራቸው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝሩን ልኮልናል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW