1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ፖለቲካሰሜን አሜሪካ

የሽግግር ሂደት ጥያቄ በኢትዮጵያ

ረቡዕ፣ ነሐሴ 1 2016

በኢትዮጵያ የሽግግር ሂደት ብሔራዊ አጀንዳ መሆን እንዳለበት የኢትዮጵያ ምሁራን እና ባለሙያዎችን መድረክ አሳስበ። መድረኩ ሰሞኑን ባካሄደው 13ኛ ጉባኤው፣ ስለ ኢትዮጵያ ፖለቲካ ባህልና የሽግግር ፈተናዎች ጥልቅ ውይይት ካካኼደ በኃላ የሽግግር ሂደት መጀመር የግድ አስፈላጊ መሆኑን አመልክቷል።

ፕሮፌሰር ሚንጋ ነጋሽ
የኢትዮጵያ ምሁራንና ባለሙያዎች መድረክ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ሚንጋ ነጋሽ ምስል Tariku Hailu/DW

የሽግግር ሂደት ጥያቄ በኢትዮጵያ

This browser does not support the audio element.

ተቀማጭነቱን በአሜሪካ ያድረገው የኢትዮጵያ ምሁራንና ባለሙያዎች መድረክ፣ ከኢትዮጵያ ምሁራን ኔትወርክ ጋር በመተባበር 13ኛ ጉባኤውን አካሄዷል። ጉባኤው  ያተኮረባቸው ነጥቦች ምንድን ናቸው በሚል፣ዶይቸ ቨለ ጥያቄ ያቀረበላቸው የመድረኩ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ሚንጋ ነጋሽ የሚከተለውን መልሰዋል።

"የፖለቲካ ባህልና የሽግግር ብለን ነው ያልነው። የፖለቲካ ባህላችን ይሆን ወይ ይህን ችግር የሚፈጥረው የሚል ሲሆን የሽግግር ፈተናዎች ሁሉጊዜም ያለ ነው።ብዙ ህዝብ እያለቀብን ነው።ረሃብ ነው፣የኢኮኖሚ ድቀት ነው ብዙ ችግሮች ነው ያሉት። በእኛ መድረክ ፣13 መሆኑ ነው እንግዲህ አንድ ሰባቱ በላይ ስብሰባዎች የተካሄዱት። እኤአ አቆጣጠር ከ2018  ማለትም አዲሱ መንግሥት ከመጣ በኋላ ነው፤ ከስድስት ዓመት በፊት ነው።ብዙ ጊዜ ሽግግሮችን እንደገና እንደገና ይነሳሉ።የምናገኛቸውም ዕድሎች እየተበላሸ፣ ከችግር ወደ ችግር እየሄደ ስለሆነ ይህንን ጉዳይ እንደገና ማጤን አለብን የሚል የሽግግር ጉዳዮች ያስፈልጋሉ የሚለውን ለማጥናት የተሞከረ ነው።"

ፕሮፌሰር ሚንጋ እንደሚሉት፣በጉባዔው ላይ ለኢትዮጵያ ይሆናሉ የተባሉ፣ ሦስት የሽግግር ሂደት አጀንዳዎች ቀርበው ውይይት ተካሄዶባቸዋል።

ለውይይት የቀረቡ የሽግግር ሂደት ሰነዶች

ከእነዚህም መኻከል አንዱ፣በአቶ ልደቱ አያሌው አቅራቢነት ውይይት የተካሄደበት ሁሉን አቀፍ የሽግግር ሂደት ሰነድ ነው።

በጦርነት ከጥቅም ውጪ የሆነ ታንክ በሑመራ ምስል Baz Ratner/REUTERS

ታዋቂው ፖለቲከኛ አቶ ልደቱ አያሌው፣በቅርቡ ሃገሪቱን ከጥፋት የሚታደግ ያሉትን የሽግግር ሠነድ ይፋ ማድረጋቸው ይታወቃል።

የአቶ ልደቱ አያሌው አዲሱ ሰነድና የኢትዮጵያ ፖለቲካ

ሌሎች በጉባዔው ላይ የተነሱና ሽግግር ላይ ያተኮሩ አጀንዳዎችን በተመለከተ፣ የመድረኩ ሊቀመንበር ያስረዳሉ።

"ዜጋ ተኮር የሽግግር ፕላን ነው የነበረው።እሱ ዳጎስ ያለ ጽሑፍ ብዙ ጊዜ ኮንሰፕት ላይ የሚደረግ ስለሆነ፣እሱን በቀላሉ ሕዝብ እንዲረዳው በዐማርኛ ቀርቧል።ከእዛም በሚቀጥለው ላይ፣ሴቭ ኢትዮጵያ በሚል የኢትዮጵያን የሽግግር ቢሆነኝ፣ እንዲሆን ቢሆን እንደዛ ቢሆን የሚል ዕቅድ ነው የሚያቀርበው፤ሠፊ ውይይት ጥያቄና መልስ ተደርጎበታል።"

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ባህል

በኢትዮጵያ ያለው የፖለቲካ ባህል ችግር እንዳለበት ጉባዔው በጥልቀት እንደመከረበትም ከፕሮፌሰር ሚንጋ ገለጻ ለመረዳት ተችሏል።

የኢትዮጵያ ፖለቲካ መዋቅራዊ መዛቦቶች እና መፍትሔያቸው

" የፖለቲካ ባህላችን ችግር እንዳለው፣በደንብ የተቀመጠ ጉዳይ ነው።በተለይ ይኼ ተምሬያለሁ  የሚለው ህዝብ ከስልጣን ጋር ያለው ቁርኝት ምን እንደሆነ፣ሃገሪቱን ወደፊት ማራመድ አለመቻሉ፣ምን ያህል ለእዛም በአብዛኛው ያለው እንደውም  እንግዳ ሆነው ተናጋሪዎች የነበሩት፣ይህንን ነገር የተመለከቱት፣ ከስነ ምግባር፣ከይሉኝታ ከኡቡንቱ  አንፃር ነው የሄዱት እና የፐብሊክ ሰርቪስ ስሜት አለመኖሩ፣ውሸት መብዛቱ በብዙ ቦታ ላይ ነተግሯል።

አቶ ልደቱ አያሌው ያቀረቡት ምክረ ሐሳብ ውይይት ከተደረገባቸው መካከል አንዱ ነው። ምስል privat

ጉባዔተኞቹ፣በኢትዮጵያ የሽግግር ሂደት ብሔራዊ አጀንዳ መሆን አለበት የሚል መግባባት ላይ መድረሳቸውን የመድረኩ ፕሬዚዳንት ገልጸዋል።

"በሁለተኛ ደረጃ ያለው ምንድነው የሽግግር ጊዜ ግድ ነው አሁን።"

በኢትዮጵያ የሽግግር መንግስት ምስረታ ጉዳይ፣በመንግስት ተቀባይነት ያለው ዐሳብ አይደለም።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አዲስ አበባ ውስጥ በቅርቡ በተካሄደው፣ የኢትዮጵያ ሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን መክፈቻ ስነስርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር፣"በኢትዮጵያ ከእንግዲህ የሽግግር መንግስት እንደማይኖር፣ሃገሪቱ ውስጥ የሚኖረው በምርጫ የተመረጠ  መንግስት ብቻ ነው።"ማለታቸው አይዘገጋም።

ታሪኩ ኃይሉ
እሸቴ በቀለ
ሸዋዬ ለገሠ 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW