1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የቀርካሃ ዛፍ ይዞታ እና ጠቃሜታው

ነጋሣ ደሳለኝ
ረቡዕ፣ መስከረም 28 2018

የክልሉ አካባቢ ጥበቃ ቢሮ እንዳለው በክልሉ ቀርካሃ ለጣውላ፣ለበር፣ ለወለል ንጣፍና ሌሎች አገልግሎቶች ጥቅም ላይ ይውላል፤ማኅበረሰቡም በምግብነት ይጠቀምበታል፡፡ በአሁኑ ወቅት በገበያ ላይ ተፈላጊነቱ በመጨመሩና በዘርፉ የተሰማሩት ባለብቶችም ቁጥር በማደጉ ቀርካሃን በጥሬው ወደ ውጭ ለመላክ ቅድመ ዝግጅች እየተደረገ እንደሆነ ተናግrሯል፡፡

የቀርካሃ ዛፍ በአሶሳ ከተማ
የቀርካሃ ዛፍ በአሶሳ ከተማ ምስል፦ Negassa Desalegn/DW

የቀርካሃ ዛፍ ይዞታ እና ጠቃሜታው

This browser does not support the audio element.

በኢትዮጵያ ቀርካሃ በስፋት ከሚገኝባቸው አካባቢዎች መካከልየቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል፡፡ በኢትዮጵያ ይገኛል ከተባለው 1.4 ሚሊዩን ሄክታር የሚሸፍን ቀርካሃ መካከል በክልሉ 9 መቶ 40ሺ ያህል ሄክታር ቀርካሃ ዛፍ እንደሚገኝ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአካባቢ ጥበቃ ቢሮ አመልክተዋል፡፡ ቀርካሃን በአሁኑ ወቅት ለውጪ ሀገር ገበያ ለማቅረብም ባለሀብቶች በዘርፉ መሰማራታቸው ተገልጸዋል፡፡ ከዚህ ደቀም  ቀርካሃን ከአጥር እና ቤት መስሪያ ብቻ ያገለግል እንደነበር ያመለከተው ክልሉ አካባቢ ጥበቃ ቢሮ የተሻለ ጥቅም እንዲሰጥ ወጭ ገበያ በስፋት ለማቅረብ እየተሰራ እንደሚገኝ ተገልጸዋል፡፡

‹‹በክልሉ 9 መቶ 40 ሺ ሄክታር ቀርካሃ ይገኛል››

 በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የቀርካሀ ዛፍን ጨምሮ የምጣኔ ሀብት ጠቃሜታ ያላቸው  ልዩ ልዩ የተፈጥሮ ዛፎችን እንደሚገኙ የገለጸው የክልሉ የአካባቢ ጥበቃ ቢሮበተለይም እንደ ቀርካሃ ያሉ ጠቀሜታቸው የጎላ ዛፎችን ለውጭ ገበያ ለማቅረብ ባለሀበቶች እየተሳተፉ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡ ለቤት ማስዋቢያና ለተለያዩ ጉዳዩች አገልግሎት ላይ የሚውለው ቀርካሃ ከዚህ ቀደም ዛፉ በክልሉ በብዛት ከመገኘቱ አንጻር አሰራሩ ባለመዘመኑ  የህብረተሰቡ ተጠቃሚነት አናሳ መሆኑን የክልሉ አካባቢ ጥበቃ ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሉቁማን አብዱልቃድር አብራርተዋል፡፡ በክልሉ የሚገኘው ቀርካሃ ጠንካራ ከሚባሉት የቆላ ቀርካዎች የሚመደብ ሲሆን  ለጣውላ፣ለበር፣ ለወለል ንጣፍና ሌሎች አገልግሎቶች በጥቅም ላይ እንደሚውም ገልጸዋል፡፡ 

የቀርካሃ ዛፍ በአሶሳ ከተማምስል፦ Negassa Desalegn/DW

‹‹ባለፈው ክረምት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ 2.3 ሚሊዩን ቀርካሃ ተተክለዋል››

በክልሉ ከሚገኙት የቤኒሻንጉል ማህረሰብ ዘንድ ለምግብነት አገልግሎት ላይ እንደሚውል የተናገሩት ኃላፊው ከዚህ በተጨማሪ በክልሉ ቀርካሀ ለቤት እና አጥር መስሪያነት በዘለለ አገልግሎት እንዳልነበረው አመልክተዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በገበያ ላይ ተፈላጊነቱ በመጨመሩና በዘርፉ የተሰማሩት ባለብቶችም ቁጥር በማደጉ ቀርካሃን በጥሬው  ወደ ውጭ ለመላክ ቅድመ ዝግጅች እየተደረገ እንደሚገኑ ተናግረዋል፡፡ የቀርካሀ ዛፍ እንዳይጠፋ በዚህ ዓመት 2.3 ሚሊዩን የቀርካሀ ችግኝ በክልሉ መተከሉን አቶ ሉቁማን አብዱልቃድር አስታውቋል፡፡ በክልሉ ብቸኛው የሆነው ባምቡ እስታር የተባለ የቀርካሀ ፋብሪካም ቀርካሀን ወደ ተለያዩ መገልገያዎች በመቀየር ስራ ላይ ተሰማርቶ ይገኛል፡፡

‹‹የቀርካሀ ውጤት ኤክስፖርት ይደረጋል››

በአሶሳ ከተማ ውስጥ የሚገኘው ባምቡ እስታር አግሮ ፎረስቴሪ የተባለው የቀርካሀ ፋብሪካም የቀርካሀ ምርቶችን ለውጭ ሀገርና ለሀገር ውስጥ ገበያዎች በማቅረብ በክልሉ  የመጀመሪያው ሲሆን በአሁኑ ወቅትም በማምረት ላይ ይገኛል፡፡ የባምቡ እስታር አግሮ ፎረስተሪ ስራ አስኪያጅ የሆኑት አሚናት ሰይድ ፋብሪካው የቀርካሃ ውጤቶችን ለመንግስትና ለግል ተቋማት በማረቅብ ላይ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡ ከዚህ ቀደም ምርቶችን ወደ ውጭ ሀገር ይልክ እንደነበር ገልጸው በአሁኑ ወቅትም አዲስ አበባን ጨምሮ ወደተለያዩ ቦታዎች የቀርካሀ ውጤቶችን እንደሚላክ አብራርተዋል፡፡
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ማዕድናትን ጨምሮ በርካታ የምጣኔ ሀብት ጠቃሜታ ያላቸው የተፈጥሮ ሀብቶች እንደሚገኙ የክልሉ የአካባቢ ጥበቃ ቢሮ መረጃ ያመለክታል፡፡ 
ነጋሳ ደሳለኝ
ኂሩት መለሰ
ፀሐይ ደሳለኝ 
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ
ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW