የቀይ መስቀል ድጋፍ በአማራ ክልል
ቅዳሜ፣ መስከረም 3 2018
በአማራ ክልል በተፈጠሮና በሠው ሠራሽ ምክንያቶች በርካቶች ለኢኮኖሚና ማህበራዊ ችግሮች ተዳርገዋል፣ ለነኚህ የህብረተሰብ ክፍሎች እርዳታና እገዛ ከሚያደርጉ ተቋማት መካክል ቀይ መስቀል ማህበር አንዱ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበርየአማራ ክልል ቅርንጫፍ ኃላፊ አቶ ሻምበል ዋለ ለዶይቼ ቬሌ አንዳስረዱት በክልሉ በተለያዩ ምክንያቶች ለችግር ለተጋለጡ 2 ሚሊዮን ለሚጠጉ አካላት ባለፉት ሁለት ዓመታት ተቋሙ ከአንድ ቢሊዮን፣ 500 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ደግፏል፡፡
በአማራ ክልል 2 ሚሊዮን ለሚሆኑ ወገኖች ድጋፍ ተደርጓል
በክልሉ በዋናንት ለተርጂነት የሚያጋልጡ ምክንያቶች ሠው ሠራሽና የተፈጠሮ ክስተቶች መሆናቸውን ያብራሩልን አቶ ሻምበል፣ በአየር መዛባት የሚከሰት ድርቀ፣ ጎርፍና በረዶ፣ በግጭቶችና ጦርነቶች የሚፈጠሩ መፈናቀሎችና የንብርተ ውድመት ተጠቃሾች እንደሆኑም አስረድተዋል፡፡ በነኚህ አደጋዎች ምክንያት በአማራ ክልል፣ “ በአጠቃላይ በግርጎሮሳዊያን አቆጣጠር በ2024/25 አንድ ቢሊዮን 700 ሚሊዮን ብር ወጪ በማድረግ 1 ሚሊዮን 900ሺህ ሠዎችን ለመደገፍ ጥረት ተደርጓል” ብለዋል፡፡
በዚህ ዓመት በሰሜንና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች ሰብላቸው በበረዶ ለወደመባቸው አርሶ አደሮችም የዘርና የገንዘብ ድጋፍ መደረጉን ኃላፊው አመልክተዋል፡፡“ብለዋል ስብላቸው በበረዶ ለወደማባቸ አርሶ አደሮች የ24 ሚሊዮን ድጋፍ ተደርጓል”ሻምበል ዋለ፣ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ቀይ መስቀል ማህበር ኃላፊ ።በዚህም 24 ሚሊዮን ብር ወጪ በማድረግ ቀይ መስቀል የምርጥ ዘርና የገንዝብ ድጋፍ አድርጓል ነው ያሉት፡ ድጋፍ ከተደረገላቸው አርሶ አደሮች መካክል በሰሜን ጎጃም ዞን፣ ሜጫ ወረዳ የአዲስ አምባ ቀበሌ ነዋሪ ቄስ ምንተስኖት ተላከ አንዱ ናቸው፡፡ለስብላቸው ለተጎዳባቸው 505 አርሶ አደሮች የስንዴ ድጋፍ፣ ለ130 አርሶ አደሮች ደግሞ ለእያንዳንዱ የ30ሺህ ብር ድጋፍ ተደርጓል ሲሉ ነው ለዶይቼ ቬሌ የገለፁት፡፡በምዕራብ ጎጃም ዞን ሰከላ ወረዳ ከለለቻ ቀበሌ አርሶ አደር አቶ አሸነፍ ፈጠነም ቀይ መስቀል ማህበር ያደረገላቸውን ድጋፍ እንደዚህ አስረድተዋል፡፡
የምርጥ ዘርና የገንዘብ ድጋፍ
“በመጀመሪያው ዙር ለእያንዳንዳችን 25 ኪሎ የስንዴ ምርጥ ዘር፣ በሁለተኛው ዙር ደግሞ የ50 ኪሎ ምርጥ ዘር ድጋፍ ተደርጎልናል፣ 10፣10ሺህ ብር ድጋፍም ተደርጎልናል፡፡” ነው ያሉት፡፡በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው ከነበሩ ተቋማት መካክል የጤና ተቋማትይጠቀሳሉ፣ በመልሶ ግንባታ፣ በምድኃኒት አቅርቦትና በስልጠና ቀይ መስቀል ማህበር ጉልህ ድርሻ እንደተወጣ የገለፁልን በደቡብ ጎንደር ዞን የጉና ቤጌምድር ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የፕሮጀክቶች አስተባባሪ አቶ እነዬ በሬ ናቸው፡፡
የመድኃኒትና ይህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ
ክምር ድንጋይ ከተማ 3.5 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የእናቶች ማቆያ፣ አምጃየ ጤና ጣቢያ ላይ በ15 ሚሊዮን ብር የሶላር ኢንርጂ ተገጥሞ ሙሉ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን እንዲሁም አልትራ ሳውንድን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ለጤና አገልግሎት የሚውሉ ቁሳቁሶችንና መድኃኒቶችን ቀይ መስቀል ድጋፍ ማድረጉን አቶ እነየ ነግረውናል፡፡
በሰሜን ወሎ ዞን የጃራ ተፈናቃዮች ጣቢያአስተባባሪ አቶ አህመድ የሱፍ ቀይ መስቀል ባለፈው ዓመት የገንዝብ ድጋፍ ማድረጉንና በቋሚነት አምቡላንስ መድቦ ህሙማንን እያገዘ መሆኑን ተናግረዋል፡፡በዝቀተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ወግኖችን በማደራጀት ራሳቸውን እንዲችሉ ተቋሙ ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገላቸው እንደሆነ ደግሞ የገለፁልን ተደራጅተው በራስ አገዝ ሥራ ተሳታፊ የሆኑት የደቡብ ወሎ ዞን ደሴ ዙሪያ ወረዳ ነዋሪ ወ/ሮ ሉባባ አህመድ ናቸው፡፡
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አማራ ቅርንጫፍ ባለፉት ሁለት ዓመታት ለ47ሺህ 967 ሠዎች ምግብ ነክና ምግብ ነክ ያልሆኑ እርዳታዎችን ሰጥቷል፣ ለ52ሺህ 683 ህሙማን የአምቡላንስ አገልግሎት ሰጥቷል፣ ለ58ሺህ 320 ግለሰቦች የገንዝብ ድጋፍ አድርጓል፡፡ እንደ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ መረጃ ተቋሙ በክልሉ 60 የውሀ ተቋማትን የገነባ ሲሆን፣ ለ120 የጤና ተቋማት ደግሞ የህክምና ቁሳቁሶችን አቅርቧል፡፡
ዓለምነው መኮንን
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ፀሀይ ጫኔ