1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቀይ ባህር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ለዓለም አቀፍ ማሕበረሰብ ያቀረበው ጥሪ

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 21 2016

የኤርትራን መንግስት ሲታገል ሁለት አሥርት ዓመታት ማሳለፉን የሚገልፀው የቀይ ባሕር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት በኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ እና የመን የሚገኙ የቀይ ባሕር አፋር ስደተኞች መብት እንዲከበርላቸው ጠየቀ። ድርጅቱ ሰሞኑን ልዩ ጉባኤ ካካሄደ በኋላ ባወጣው መግለጫ የኤርትራን መንግሥት በመንኛውም ሁኔታ ከስልጣን ለማንሳት አቋም መያዙን ጠቅሷል።

Die Mitglieder des Red Sea Afar Organisationskomitees
ምስል Solomon Muchie/DW

የቀይ ባህር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ለዓለም አቀፍ ማሕበረሰብ ያቀረበው ጥሪ

This browser does not support the audio element.

የቀይ ባህር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ለዓለም አቀፍ ማሕበረሰብ ያቀረበው ጥሪ 

የኤርትራን መንግስት ሲታገል ሁለት አሥርት ዓመታት ማሳለፉን የሚገልፀው የቀይ ባሕር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት በኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ እና የመን የሚገኙ የቀይ ባሕር አፋር ስደተኞች መብት እንዲከበርላቸው ጠየቀ። ድርጅቱ ሰሞኑን ልዩ ጉባኤ ካካሄደ በኋላ ባወጣው መግለጫ የኤርትራን መንግሥት በመንኛውም ሁኔታ ከስልጣን ለማንሳት አቋም መያዙን ጠቅሷል። ድርጅቱ ለዚህ አቋሙ መነሻ ነው ያለው ሁሉም የኤርትራ ሕዝቦች በተለይም የቀይ ባሕር አፋር ሕዝብ ለአስከፊ ጫና እና ስደት መዳረጉ ነው። 

የድርጅቱ ውይይትና ያወጣው አቋም 

የቀይ ባሕር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ማዕከላዊ ኮሚቴ ከቀናት በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ ስብሰባ ማድረጉንና በኤርትራ የፖለቲካ፣ የደኅንነት፣ የኢኮኖሚ እና ሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ዙሪያ መነጋገሩን ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል። የቀይ ባሕር አፋር ሕዝብ በተለየ ሁኔታ ከፍተኛ "መገለል እና በደል እየደረሰበት ነው" የሚለው ድርጅቱ፣ ያለፉት ስድስት ዓመታት በትግል ሂደቱ የገጠሙት ፈታኝ ወቅቶች መሆናቸውን ገልጿል። ይህም በመሆኑ ድርጅቱ የኤርትራን መንግስት በተባበረ ጥረት ማስወገድ የሚል አቋም መያዙን የድርጅቱ የውጭ ጉዳይ ግንኙነት ምክትል ኃላፊ እና የሊቀመንበሩ አማካሪ አቶ ነስረዲን አሕመድ ለዶቼ ቬለ  ተናግረዋል።  

የቀይ ባሕር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ማዕከላዊ ኮሚቴ ከቀናት በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ ስብሰባ ማድረጉንና በኤርትራ የፖለቲካ፣ የደኅንነት፣ የኢኮኖሚ እና ሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ዙሪያ መነጋገሩን ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል።ምስል Solomon Muchie/DW

 

"የቀይ ባሕር አፋር ሕዝብ ሃይለኛ ጭቆና እንደወረደበት፣ በስደትም ይሁን እዛም ሀገሩ ውስጥ ላይ ብዙ ችግሮችን ያጋጠመው መሆናቸው.... የባሕር በር ያለው በቀጣናው ሰላም እና ዕድገት መስመጣት የሚችል ሕብረተሰብ በመሆኑ ትኩረት ተሰጥቶ መብቶቹ እንዲከበሩ" እንዲታገዝ ነው የምንፈልገው ብለዋል። 

የኤርትራን መንግስት በፖለቲካ እና ወታደራዊ አማራጮች የሚታገል መሆኑን የሚገልፀው ይህ ድርጅት፣ ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ለስደተኛ ኤርትራዊያን ጥገኝነት ጠያቂዎች ሕጋዊ ከለላ እንዲያገኙ እንዲያስችል፣ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ማስተባበሪያ ቢሮም እነዚህን ስደተኞች ኑሮ መስርተው ሊኖሩ ወደሚችሉባቸው ሦስተኛ ሀገራት እንዲያዘዋውር የድርጅቱ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ያሲን መሐመድ አብደላ ጠይቀዋል። 

የቀይ ባህር አፋር ድርጅት መግለጫ

"ስደተኞች ተመዝግበዋል በኢትዮጵያም። እስከ 70 ሺህ የሚጠጋ ስደተኛ አለ። ጅቡቲም እንደዚሁ። የመንም እንደዚሁ። ምዝገባ እያደረጉ ሕጋዊነት እንዲሰጣቸው፣ በተመዘገቡበት አካባቢ የምግብ፣ የመጠለያ፣ የልጆች የመማር፣....እንደዚህ አይነት ነገሮች ከፍትኛ እጥረት አለ"። 

የኤርትራ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በአስከፊ ሥርዓት ውስጥ መሆናቸውን የሚገልፀው የቀይ ባሕር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ይህ ችግር እስኪስተካከል ድረስ ሁሉን አቀፍ ትግል ማድረጉን እንደሚቀጥል በመግለጫቸው አስታውቋል።

ሰለሞን ሙጬ 

አዜብ ታደሰ 

ማንተጋፍቶት ስለሺ 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW