የቀድሞዋ ንግስት ኤልሳቤት ዳግማዊት የንግስናቸው ታሪካዊ ዳራ እና ወራሻቸው
ሰኞ፣ መስከረም 2 2015
ማስታወቂያ
የታላቋ ብሪታንያ ንግስት ኤልሳቤት ዳግማዊት ከዚህ ዓለም በሞት የመለየታቸው ዜና የተሰማው ባለፈው ሐሙስ ነበር ። 96 ዓመታቸው ነበር ። ንግስት ኤልሳቤት በታላቋ ብሪታንያ እና በሌሎች የጋራ ብልጽግና ሀገራት ያለፉትን 70 ዓመታት በንግስና ቆይተዋል። የንግስትቱን ህልፈት ተከትሎ የሀገሪቱ ህገ መንግስት በሚደነግገው መሰረት የበኩር ልጃቸው ልዑል ቻርለስ ሳልሳዊ በትረ ዙፋኑን ተረክበው የንግስና ስነ ስረዓታቸውን ባለፈው ቅዳሜ ፈጽመዋል። የእናታቸው የቀድሞዋ ንግስት ኤልሳቤት ዳግማዊ የቀብር ስነ ስረዓት የሚከናወንበትን ቀን እና ሂደት በማሳወቅ የንግስና ስራቸውን አንድ ብለው ጀምረዋል። የቀድሞዋ ንግስት ኤልሳቤት ዳግማዊት በህይወት ዘመናቸው ኢትዮጵያን ጨምረው የተለያዩ የዓለም ሀገራትን ግብኝተዋል። የንግስቲቱ ሕልፈ,ት በታላቋ ብሪታንያ የተለያዩ ለውጦችን ሊስከትል እንደሚችል ይነገራል። የንግስቲቱን ወደ ንግስና የመጡበትን ታሪካዊ ዳራ ፤ በተለያዩ የዓለም ሃገራት ያደረጓቸውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶችን እና ሌሎችን ቤተሰባዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የለንደኑ ወኪላችን ድል ነሳ ጌታነህ ያሰናዳውን የዕለቱን ማህደረ ዜና እነሆ ብለናል ።
ድል ነሳ ጌታነህ
ታምራት ዲንሳ
ኂሩት መለሰ