1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የቀድሞው የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኒኮላ ሳርኮዚ ከእስር ተፈቱ

ሰኞ፣ ኅዳር 1 2018

የአምስት ዓመት እስር ተፈርዶባቸው ባለፈው መስከረም ላ ሶንት የተባለ እስር ቤት ከወረዱ 20 ቀን የሆናቸው ሳርኮዚ ተለቀው ዛሬ ቤታቸው ገብተዋል። የ70 ዓመቱ ሳርኮዚ በመስከረም የተበየነባቸውን የ5 ዓመት እስር ከጀመሩ ከሳምንታት በኋላ ዛሬ ጠዋት ነበር ከእስር እንዲለቀቁ ለፍርድ ቤቱ ይግባኝ ያሉት። ሳርኮዚ ዛሬ ከእስር የተለቀቁት በገደብ ነው።

ኒኮላ ሳርኮዚከታሰሩበት ላ ሶንት እስር ቤት በመኪና ሲወጡ
ኒኮላ ሳርኮዚ ከታሰሩበት ላ ሶንት እስር ቤት በመኪና ሲወጡምስል፦ Raphael Lafargue/ABACAPRESS/IMAGO

ኒኮላ ሳርኮዚ ከእስር ተፈቱ

This browser does not support the audio element.

ዛሬ ያስቻለው አንድ የፓሪስ ፍርድ ቤት የቀድሞው የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኒኮላ ሳርኮዚ  ከእስር እንዲለቀቁ ወሰነ። የአምስት ዓመት እስር ተፈርዶባቸው ባለፈው መስከረም ላ ሶንት የተባለ እስር ቤት ከወረዱ 20 ቀን የሆናቸውሳርኮዚ ከእስር ተለቀው ዛሬ ቤታቸው ገብተዋል።  የ70 ዓመቱ ሳርኮዚ በመስከረም የተበየነባቸውን የአምስት ዓመት እስር ከጀመሩ ከሳምንታት በኋላ ዛሬ ጠዋት ነበር ከእስር እንዲለቀቁ ለፍርድ ቤቱ ይግባኝ ያሉት። ሳርኮዚ ዛሬ ከእስር የተለቀቁት በገደብ ነው።

የታሰሩትም በጎርጎሮሳዊው 2007 ዓም ለተካሄደው የፈረንሳይ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የቅርብ ረዳቶቻቸው ከቀድሞ የሊቢያ ፕሬዝዳንት ሞአመር ጋዳፊ ባካሄዱት ገንዘብ የማሰባሰብ ሙከራ፣ በወንጀል ሴራ ጥፋተኛ ከተባሉ በኋላ ተፈርዶባቸው ነው። የቀድሞው ወግ አጥባቂፕሬዝዳንት ሳርኮዚ ባለፈው መስከረም የአምስት ዓመት እስር ሲበየንባቸው በእለቱም ሆነ ከዚያም በፊት ምንም ስህተት እንዳልፈፀሙ በተደጋጋሚ ሲናገሩ ቆይተዋል። የበቀልና የጥላቻ ሰለባ ሆኛለሁ ሲሉም በምሬት ገልጸው ነበር ።

ኒኮላ ሳርኮዚ ከእስር ተፈተው ቤታቸው እንደደረሱ ምስል፦ Geoffroy Van Der Hasselt/AFP

 ፈረንሳይን ከጎርጎሮሳዊው 2007ዓ.ም. እስከ 2011 ዓም የመሩት ሳርኮዚ በፈረንሳይ ፕሬዝዳንቶች የቅርብ ጊዜ ታሪክ ዘብጥያ የወረዱ የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት ናቸው። ስለ ሳርኮዚ ዛሬ ከእስር  መለቀቅ የፓሪስዋን ዘጋቢያችንን ሃይማኖት ጥሩነህን ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግረናታል።

 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ
ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW