1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቀድሞ የሄይቲ አምባገነን መሪ ወደ ትውልድ ሀገራቸው መመለስ

ማክሰኞ፣ ጥር 10 2003

በስደት ፈረንሳይ ሀገር የነበሩት የቀድሞ የሀይቲ አምባገነን መሪ ዦን ክሎድ ዲውቫልየ ከትናንት በስቲያ ወደ ትውልድ ሀገራቸው ተመለሱ።

ምስል AP

ለስድሳ ሺህ የሄይቲ ዜጎች ሞት ተጠያቂ የሚባሉት ዲውቫልየ እአአ በ 1986 ዓም በሀገራቸው በተነሳ የህዝብ ዓመጽ ሰበብ ነበር መሰደድ የተገደዱት። የዶይቸ ቬለ ባልደረባ ማርቲን ፖላንስኪ እንደዘገበው፡ በብዙ ሚልዮን የሚገመት የሀገሪቱን ሀብት ለራሳቸው ማበልጸጊያም ተጠቅመውበታል የሚባሉት ዲውቫልየ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ያስከተለባትን ከፍተኛ ጥፋት ለመቋቋም በመታገል ላይ ወዳለችው እና ባለፈው ህዳር ወር የተካሄደው የመጀመሪያው ዙር ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ውጤት አሁንም እያወዛገበ ወዳለባት ድሀይቱ ሀገር ሄይቲ በአሁኑ ጊዜ መመለሳቸው ብዙ እያጠያየቀ ነው።

ማርቲን ፖላንስኪ

አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW