የቀድሞ የሶማሌ ክልል ባለሥልጣናት ታሰሩ
ሐሙስ፣ ነሐሴ 13 2013![Somali Regional Police Logo](https://static.dw.com/image/58909735_800.webp)
ማስታወቂያ
የሶማሌ ክልል እና አጎራባች አካባቢዎች ሁከት እና ብጥብጥ እንዲፈጠር ሲሰሩ ነበር የተባሉ አካላት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰማ። የክልሉ ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ያዋላቸው ተጠርጣሪዎች ቀደም ሲል በክልል ደረጃ በሥልጣን ላይ የነበሩ እንደሆኑ መረጃውን ለዶቼ ቬለ ያረጋገጡት የሶማሌ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር እና የወንጀል መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት በክልሉ የፀጥታ ስጋት እንደሌለ በማመልከትም የፀጥታ ኃይሉ ከሚወስደው ርምጃ በተጨማሪ ኅብረተሰቡ ከዚህ ቀደም የደረሱ አስከፊ ችግሮች እንዳይደገሙ ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በመተባበር እየሠራ ነውም ብለዋል።
መሳይ ተክሉ
ሸዋዬ ለገሠ
አዜብ ታደሰ