የቀድሞ የጦር መኮንን አስተያየት
ማክሰኞ፣ ጥቅምት 2 2014
ማስታወቂያ
ሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕወሓት) «ተከፈተብኝ» ያለዉን ጥቃት የኢትዮጵያ መንግስት እስካሁን በይፋ አላረጋገጠም።ይሁንና የጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አሕመድ ቃል አቀባይ ቢልለኔ ስዩም አሶስየትድ ፕረስ ለተባለዉ ዜና አገልግሎት፣ ሕወሓት በአማራና በሌሎች አካባቢዎች ያደርሰዋል ያሉትን ጥፋት፣ጥቃትና ግድያን ለማስቆም የኢትዮጵያ መንግስት መጣሩን ይቀጥላል ብለዋል።ቃል አቀባይዋን በስልክ ለማግኘት በተደጋጋሚ ብንሞክርም ስልካቸዉን አይመልሱም።የሕወሓት ቃል አቀባይን ለማነጋገር ያደርግነዉ ሙከራም አልተሳካም።የኢትዮጵያ መከላከያ ሚንስቴር ትናንት በፌስ ቡክ ገፁ ባወጣዉ መግለጫ ግን "ሠራዊቱ በራሱ እቅድ ሙሉ ማጥቃት ከጀመረ 'ተጠቃሁ' ብሎ ለመናገር ጊዜ እንኳን ሳያገኝ የሚፈፀም እንደሚሆን መታወቅ አለበት" ብሎ ነበር። መግለጫዉ ዛሬ ከየገፁ ተነስቷል ወይም ተሰርዟል።
ሰለሞን ሙጬ
ነጋሽ መሐመድ
ኂሩት መለሰ