የቀጠለው የህዳሴው ግድብ ውዝግብ
ሰኞ፣ የካቲት 1 2013
ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ በመጪው ሐምሌ የታላቁ ህዳሴ ግድብ የውኃ ሙሌትን በተናጠል ውሳኔዋ የምትሞላ ከሆነ የሀገሯ ብሔራዊ ደህንነት ቀጥተኛ ሥጋት አድርጋ እንደምትወስደው ሱዳን አስታወቀች። የሀገሪቱ የመስኖ እና ውኃ ሃብት ሚኒስትሩ እንዳሉት ሱዳን የግድቡ የሦስትዮሽ ድርድር ላይ አሜሪካ፣ የአውሮጳ ሕብረት፣ የተባበሩት መንግሥታትና የአፍሪካ ሕብረት የማደራደር ሚና እንዲኖራቸው አቋም መያዟንም ገልፃለች። የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ ሁሌም እንደሚለው የታችኛው የተፋሰሱ ሃገራትን ጥቅም ሳይጎዳ የኢትዮጵያዊያንን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የሚሠራው ግድብ ላይ ሁለቱ ሃገራት ስምምነት ላይ የመድረስ ፍላጎት እንደሌላቸው እየታየ መሆኑን አስታውቋል።
ሰሎሞን ሙጬ
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ